መላው ዓለም ከእርስዋ ጠጥቶ ይሰክር ዘንድ ባቢሎን በእኔ እጅ እንደ ወርቅ ዋንጫ ነበረች፤ አሕዛብ ሁሉ የእርስዋን ወይን ጠጅ ጠጥተው አእምሮአቸውን ሳቱ።
ዳንኤል 3:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ወገኖች፥ ከልዩ ልዩ ሀገር የመጡ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ሁሉ የመለከትና፥ የእንቢልታ፥ የመሰንቆና፥ የክራር፥ የበገና፥ የዋሽንትና የሙዚቃ ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ በመሬት ላይ ተደፍተው ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል ሰገዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የመለከትና የእንቢልታ፣ የመሰንቆና የክራር፣ የበገናና የዋሽንት፣ የዘፈንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ሕዝቡ ሁሉ፣ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች፣ ንጉሥ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል ተደፍተው ሰገዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፥ የመሰንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፥ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ። |
መላው ዓለም ከእርስዋ ጠጥቶ ይሰክር ዘንድ ባቢሎን በእኔ እጅ እንደ ወርቅ ዋንጫ ነበረች፤ አሕዛብ ሁሉ የእርስዋን ወይን ጠጅ ጠጥተው አእምሮአቸውን ሳቱ።
ንጉሥ ሆይ! አንተ የመለከት፥ የእንቢልታ፥ የመሰንቆ፥ የክራር፥ የበገናና የዋሽንት፥ የሙዚቃ ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ማናቸውም ሰው በመሬት ላይ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል እንዲሰግድ ዐዋጅ አውጥተህ ነበር።
በዚያን ጊዜ አንድ ዐዋጅ ነጋሪ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ከልዩ ልዩ ሀገር የመጣችሁ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የምትናገሩ ነገዶች ሆይ!
የመለከት የእንቢልታ የመሰንቆ የክራር፥ የበገና፥ የዋሽንት፥ የሙዚቃ ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ በምድር ላይ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል እንድትሰግዱ ታዛችኋል።
ታላቁም ዘንዶ ወደታች ተጣለ፤ እርሱ መላውን ዓለም የሚያስተው ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው እባብ ነው። እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።
በመጀመሪያው አውሬ ፊት እንዲያደርግ በተፈቀደለት ተአምራት ምክንያት በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያስት ነበር፤ በሰይፍ ቈስሎ ለዳነው ለአውሬው ክብር ምስል እንዲሠሩም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዛቸዋል።
ከአውሬው ራሶች አንዱ ለሞት የሚያደርስ ቊስል እንደ ነበረው ሆኖ አየሁት፤ ነገር ግን ለሞት የሚያደርሰው ቊስሉ ድኖአል፤ ዓለም በሙሉ በመደነቅ አውሬውን ተከተለ።
ያየኸው አውሬ ቀድሞ ነበር፤ አሁን የለም፤ በኋላ ከጥልቁ ጒድጓድ ይወጣል፤ ወደ ጥፋቱም ይሄዳል፤ ዓለም ሲፈጠር ጀምሮ ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ የምድር ኗሪዎች፥ አውሬው ቀድሞ የነበረ፥ አሁን የሌለ፥ በኋላ የሚመጣ መሆኑን ሲያዩ ይደነቃሉ።
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።