ዳንኤል 10:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ይህን አስደናቂ ራእይ እየተመለከትኩ ብቻዬን ቀረሁ፤ የነበረኝን ኀይል ሁሉ በማጣት ደክሜ ነበር፤ ፊቴም በጣም ገረጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ይህን ታላቅ ራእይ እያየሁ ብቻዬን ቀረሁ፤ ምንም ጕልበት አልነበረኝም፤ መልኬ እጅጉን ገረጣ፤ ኀይልም አጣሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ብቻዬን ቀረሁ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፥ ኃይልም አልቀረልኝም፥ ደም ግባቴም ወደ ማሸብሸብ ተለወጠብኝ፥ ኃይልም አጣሁ። |
ከዚህ በኋላ ሰውን የሚመስለው እጁን ዘርግቶ ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤ እኔም እንዲህ አልኩት፦ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ራእይ በጣም ስላሳመመኝ ሰውነቴ ዛለ።
የሕልሙም ትርጒም እዚህ ላይ ይፈጸማል፤ እኔም ዳንኤል እጅግ ሐሳቡ አስፈራኝ፤ በመደንገጥም ፊቴ ገረጣ፤ ይሁን እንጂ ሁሉንም ነገር በልቤ ሰውሬ ያዝኩ።
እኔ ዳንኤል እጅግ ደከመኝና ሕመም ስለ ተሰማኝ ለብዙ ቀኖች ተኛሁ፤ ከዚያም በኋላ ተነሥቼ ንጉሡ በመደበልኝ ሥራ ላይ ተሰማራሁ፤ በራእዩ እጅግ ተጨነቅሁ፤ ላስተውለውም አልቻልኩም ነበር።
ወደ በጉም ሲጠጋ አየሁት፤ እርሱም በበጉ ላይ በመቈጣት መቶት ሁለት ቀንዶቹን ሰባበረበት፤ በጉም ለመቋቋም የሚያበቃው ኀይል አላገኘም፤ ስለዚህ ፍየሉ ወደ መሬት ጥሎ ረገጠው፤ ከኀይሉም ሊያድነው የሚችል አልነበረም።
ይህን ሁሉ ስሰማ ሰውነቴ ይርበደበዳል፤ ድምፁም ከንፈሮቼን ያንቀጠቅጣል፤ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼ ከታች ይብረከረካሉ፤ በጠላቶቻችን ላይ መከራ የሚደርስበትን ጊዜ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።
ይሁን እንጂ እያንዳንዳችሁ በየበኩላችሁ የምትበታተኑበትና እኔን ብቻዬን የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፤ ሰዓቱም አሁን ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።
ከነዚህ ከተገለጡልኝ ታላላቅ ነገሮች የተነሣ እንዳልታበይ ሥጋዬን እንደ እሾኽ የሚወጋ ሥቃይ ተሰጠኝ፤ ይህም የሰይጣን መልእክተኛ በመሆን እየጐሸመ በማሠቃየት እንዳልታበይ ያደርገኛል።
ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅኩ፤ እርሱ ግን ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፤ “አትፍራ፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ፤