ዳንኤል 10:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ በሐዘን ላይ ነበርኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ እኔ ዳንኤል ለሦስት ሳምንት አለቀስሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። |
ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ! አትፍራ! ማስተዋልን ለማግኘት ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማዋረድ ከወሰንክበት ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ ጸሎትህ ተሰምቶአል፤ እኔም ተልኬ ወደ አንተ የመጣሁት ጸሎትህ መልስ ከማግኘቱ የተነሣ ነው።
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እያለ ሚዜዎች ማዘን ይገባቸዋልን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ይጾማሉ።