ዳንኤል 10:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩም “በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደድክ ዳንኤል ሆይ! እነሆ፥ እኔ ወደ አንተ ተልኬ መጥቼአለሁ፤ ባለህበት ቀጥ ብለህ ቁም፤ የምነግርህንም በጥንቃቄ አስተውል!” አለኝ። ይህን በነገረኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥኩ ቆምኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “እጅግ የተወደድህ ዳንኤል ሆይ፤ አሁን ወዳንተ ተልኬአለሁና፣ የምነግርህን አስተውል፤ ቀጥ ብለህም ቁም” አለኝ። ይህን ሲለኝም፣ እየተንቀጠቀጥሁ ተነሥቼ ቆምሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ እጅግ የተወደድህ ሰው ዳንኤል ሆይ፥ እኔ ዛሬ ወደ አንተ ተልኬአለሁና የምነግርህን ቃል አስተውል፥ ቀጥ ብለህም ቁም አለኝ። ይህንም ቃል ባለኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥሁ ቆምሁ። |
እነዚያ ሦስት ሰዎች ማለትም ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ በውስጥዋ ቢገኙ እንኳ በደግነታቸው ማትረፍ የሚችሉት የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ነው፤ ይህን የተናገረ ጌታ እግዚአብሔር ነው።
እርሱም “አንተ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደድክ ሰው ሆይ! መልካም ይሆንልሃል፤ አትፍራ! አይዞህ በርታ!” አለኝ። እርሱም በተናገረኝ ጊዜ ብርታት አገኘሁና “ጌታዬ ሆይ፥ ብርታት ስለ ሰጠኸኝ እነሆ፥ ተናገር” አልኩት።
ጴጥሮስ ዘወር ብሎ ኢየሱስ የሚወድደው ደቀ መዝሙር ሲከተለው አየ፤ ይህ ደቀ መዝሙር በእራት ጊዜ ወደ ኢየሱስ ተጠግቶ፥ “ጌታ ሆይ፥ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ብሎ የጠየቀው ነው።
አሁን ግን ተነሥና በእግርህ ቁም፤ እኔ የተገለጥኩልህ አሁን እኔን ባየህበትና ወደፊትም እኔ ለአንተ በምገለጥበት ነገር አገልጋይና ምስክር እንድትሆነኝ ልሾምህ ፈልጌ ነው።