ዳንኤል 10:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ አንዳች እጅ ዳሰሰኝ፤ ገና እየተንቀጠቀጥኩ ስለ ነበር ደግፎ በእጄና በጒልበቴ እንድቆም አደረገኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆም፣ አንድ እጅ ዳሰሰኝ፤ እየተንቀጠቀጥሁም በእጄና በጕልበቴ አቆመኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ አንዲት እጅ ዳሰሰችኝ፥ በጕልበቴና በእጄም አቆመችኝ። |
ከዚህ በኋላ ሰውን የሚመስለው እጁን ዘርግቶ ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤ እኔም እንዲህ አልኩት፦ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ራእይ በጣም ስላሳመመኝ ሰውነቴ ዛለ።
በዚህም ጸሎት ላይ ሳለሁ በመጀመሪያው ራእይ ያየሁት ገብርኤል እኔ ወዳለሁበት ስፍራ በፍጥነት እየበረረ መጣ፤ ጊዜውም የሠርክ መሥዋዕት የሚቀርብበት ወቅት ነበር።
ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅኩ፤ እርሱ ግን ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፤ “አትፍራ፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ፤