Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዳንኤል 8:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እርሱም በሚናገርበት ጊዜ ኅሊናዬን ስቼ በግንባሬ ወደ መሬት ተደፋሁ፤ እርሱ ግን ዳሰሰኝና ከመሬት አንሥቶ በእግሮቼ አቆመኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እየተናገረኝ ሳለ፣ በምድር ላይ በግንባሬ ተደፋሁ፤ በከባድ እንቅልፍም ተዋጥሁ፤ እርሱ ግን ዳሰሰኝና በእግሮቼ አቆመኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሲናገረኝም ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ፥ እርሱም ዳሰሰኝ ቀጥ አድርጎም አቆመኝ።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 8:18
13 Referencias Cruzadas  

ያ ሰው የሚመስለው መልአክ እንደገና በዳሰሰኝ ጊዜ ብርታት አገኘሁ።


በዚህ ጊዜ ጴጥሮስና ጓደኞቹ በእንቅልፍ ተሸንፈው ተኝተው ነበር፤ በነቁ ጊዜ ግን የኢየሱስን ክብርና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሁለቱን ሰዎች አዩ።


ከዚህ በኋላ ሰውን የሚመስለው እጁን ዘርግቶ ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤ እኔም እንዲህ አልኩት፦ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ራእይ በጣም ስላሳመመኝ ሰውነቴ ዛለ።


በተናገረኝም ጊዜ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጤ ገብቶ በእግሮቼ አቆመኝ፤ የሚናገረኝንም ሰማሁ፤


አሁን ግን ለፍርድ እዚህ የቆምኩት እግዚአብሔር ለአባቶቻችን ስለ ሰጠው የቃል ኪዳን ተስፋ ነው።


ከጸሎቱ ተነሥቶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጣ፤ ከሐዘን ብዛት የተነሣ ተኝተው አገኛቸውና እንዲህ አላቸው፤


ያነጋግረኝ የነበረው መልአክ እንደገና መጥቶ ከእንቅልፉ እንደሚቀሰቀስ ሰው ቀሰቀሰኝ፤


እኔ ዳንኤል እጅግ ደከመኝና ሕመም ስለ ተሰማኝ ለብዙ ቀኖች ተኛሁ፤ ከዚያም በኋላ ተነሥቼ ንጉሡ በመደበልኝ ሥራ ላይ ተሰማራሁ፤ በራእዩ እጅግ ተጨነቅሁ፤ ላስተውለውም አልቻልኩም ነበር።


ገብርኤልም መጥቶ በአጠገቤ በቆመ ጊዜ ደንግጬ ወደ መሬት ወደቅኹ። እርሱም “የሰው ልጅ ሆይ! ራእዩ የሚያመለክተው ስለ ዓለም መጨረሻ መሆኑን ተረዳ” አለኝ።


ሰዎች ከባድ እንቅልፍ በሚይዛቸውና በሚያስጨንቅ የሌሊት ቅዠት ጊዜ፥


የፀሐይ መጥለቂያ ሰዓት እየተቃረበ ሲሄድ አብራምን ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እነሆ፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ መጣበት።


ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅኩ፤ እርሱ ግን ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፤ “አትፍራ፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios