አሞጽ 7:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይስሐቅና የልጅ ልጆቹ ከፍተኛ የመስገጃ ቦታዎች ይፈራርሳሉ፤ የእስራኤልም የተቀደሱ ቦታዎች ፈራርሰው ወና ይሆናሉ፤ የኢዮርብዓምን መንግሥት ፈጽሞ አጠፋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የይሥሐቅ ማምለኪያ ኰረብቶች ባድማ ይሆናሉ፤ የእስራኤል መቅደሶች ይፈርሳሉ፤ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፌ እነሣለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይስሐቅም የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፥ የእስራኤልም መቅደሶች ባድማ ይሆናሉ፤ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሣለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሳቂያ የሆኑ የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ የእስራኤልም መቅደሶች ባድማ ይሆናሉ፤ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሣለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይስሐቅም የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፥ የእስራኤልም መቅደሶች ባድማ ይሆናሉ፥ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሣለሁ አለ። |
ዳግማዊ ኢዮርብዓምም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ ከእርሱ በፊት የነበረውን የናባጥ ልጅ የኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ።
‘ስለ ተሰደብን አፈርን፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ባዕዳን ሰዎች ስለ ገቡ ተዋርደን አንገታችንን ደፋን።’ በሉ።
የእስራኤል ተራራዎች የልዑል እግዚአብሔርን ቃል እንዲሰሙ ንገራቸው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምናገረውን ተራራዎች፥ ኮረብቶችንና ገደላማ ሸለቆዎች ሁሉ ይስሙ፤ ሕዝቦች ለጣዖቶች የሚሰግዱባቸውን ከፍተኛ ቦታዎች ሁሉ የሚያጠፋ ሰይፍ እልካለሁ።
የእስራኤል ሕዝብ አዌን በተባለ ከተማ ጣዖት በማምለክ ኃጢአት የሚሠሩባቸው ከፍተኛ ቦታዎች ይፈራርሳሉ፤ በመሠዊያዎቻቸውም ላይ እሾኽና አሜከላ ይበቅሉባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ ሕዝቡ ተራራዎችን “ደብቁን!” ኮረብቶችንም “ጋርዱን!” ይላሉ።
ስለ ሠሩት ኃጢአት የእስራኤልን ሕዝብ በምቀጣበት ቀን በቤትኤል የሚገኙትን መሠዊያዎች አፈራርሳለሁ፤ የመሠዊያዎቹም ቀንዶች ተሰባብረው በምድር ላይ ይወድቃሉ።
ወደ ቤርሳቤህ አትሂዱ፤ ቤቴል ፈራርሳ እንዳልነበረች ስለምትሆን በጌልገላ የሚኖሩ ሕዝቦችም ስደት ስለ ተፈረደባቸው ወደ ቤቴልም ሆነ ወደ ጌልጌላ አትሂዱ።”
‘አሺማ’ ተብላ በምትጠራ በሰማርያ ሴት አምላክ የሚምሉ ‘በዳን አምላክ’ ወይም ‘በቤርሳቤህ አምላክ’ እያሉ የሚምሉ ሁሉ ይወድቃሉ፤ ከወደቁበትም ፈጽሞ መነሣት አይችሉም።”
እግዚአብሔርን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ ሲል አዘዘ፦ “መድረኮቹ እስኪናወጡ ድረስ የቤተ መቅደሱን ጒልላት ምታ፤ ሰባብረህም በሰዎቹ አናት ላይ እንዲደረመስ አድርግ፤ ከዚያ የተረፉትንም እኔ በሰይፍ እጨርሳቸዋለሁ፤ ማንም መሸሽ አይችልም፤ ማንም ሊያመልጥ አይችልም።
ይህ ሁሉ የሆነው እስራኤላውያን በፈጸሙት በደል ምክንያት ነው፤ የእስራኤል ሕዝብ እንዲያምፁ ምክንያት የሆነው ማን ነው? ዋና ከተማዋ ሰማርያ አይደለችምን? የይሁዳስ ሕዝብ ጣዖት በማምለክ ኃጢአት እንዲሠሩ ያደረገ ማን ነው? ኢየሩሳሌም አይደለችምን?