የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት ይሠሩለት ዘንድ አናጢዎች፥ ግንበኞችና የሊባኖስ ዛፍ እንጨት አስይዞ መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ።
አሞጽ 1:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የጢሮስ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ የገቡበትን የወንድምነት ቃል ኪዳን አፍርሰው የማረኳቸውን ሕዝቦች ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጢሮስ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም። የወንድማማችነትን ቃል ኪዳን በማፍረስ፣ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ ለኤዶም ሸጣለችና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በምርኮ የሄዱትን ሕዝብ ሁሉ ለኤዶምያስ አሳልፈው ሰጥተዋልና፥ የወንድማማቾችንም ቃል ኪዳን አላስታወሱምና ስለ ሦስት የጢሮስ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የሰሎሞን ምርኮኞችን በኤዶምያስ ዘግተዋልና፥ የወንድሞችንም ቃል ኪዳን አላሰቡምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢሮስ ኀጢአት አልመለስላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምርኮኞችን ሁሉ ለኤዶምያስ አሳልፈው ሰጥተዋልና፥ የወንድሞችንም ቃል ኪዳን አላሰቡምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢሮስ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም። |
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት ይሠሩለት ዘንድ አናጢዎች፥ ግንበኞችና የሊባኖስ ዛፍ እንጨት አስይዞ መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ።
ፍልስጥኤም የምትጠፋበት ጊዜ ደርሶአል፤ ከሞት ተርፈው ጢሮስንና ሲዶናን የሚረዱት ሁሉ ተቈራርጠው የሚቀሩበት ጊዜ ተቃርቦአል። እኔ እግዚአብሔር፥ ከሞት ተርፈው በባሕር ዳርቻ የምትገኘው የካፍቶር ዘሮች የሆኑትን ፍልስጥኤማውያን በሙሉ እደመስሳለሁ።
የንግድ ሸቀጥ ሀብትሽ ሁሉ፥ መርከብ ነጂዎችሽ ሁሉ፥ በመርከብ ውስጥ የሚያገለግሉ ጠጋኞችሽና ነጋዴዎችሽ ሁሉ፥ በመርከቢቱ ውስጥ የነበሩ ወታደሮች ሁሉ፥ መርከቦችሽ ሲሰባበሩ ሁሉም ወደ ጥልቁ ባሕር ይሰጥማሉ።
በመግዛትና በመሸጥ ከፈጸምከው በደል የተነሣ የአምልኮ ስፍራዎችህ ሁሉ ረከሱ፤ ስለዚህ በከተማይቱ የሰደድ እሳት እንዲነሣ አድርጌ በሙሉ አቃጠልኳት፤ አሁን ወደ አንተ የሚመለከቱ ሁሉ ዐመድ ብቻ መሆንክን ያያሉ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኤዶም ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ወንድሞቻቸውን እስራኤላውያንን በሰይፍ አሳደዋቸዋል፤ ከያዙአቸውም በኋላ ርኅራኄ አላደረጉላቸውም፤ በእነርሱ ላይ ያላቸው ቊጣ ሊበርድም አልቻለም፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የጋዛ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ የሀገሩን ሕዝብ ሁሉ ከማረኩ በኋላ ለኤዶም ሰዎች አሳልፈው ሰጥተዋቸዋል።
ጠላቶቻቸው በሮቻቸውን ሰባብረው፥ ሀብታቸውን ሁሉ በዘረፉበት ቀን፥ አንተ በዳር ቆመህ ትመለከት ነበር፤ አንተ እኮ ኢየሩሳሌምን በዕጣ ከተከፋፈሉአት ሰዎች በምንም አትሻልም።
“ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ተአምራት፥ በጢሮስና በሲዶና ከተሞች ተደርገው ቢሆን ኖሮ በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የሐዘን ልብስ ለብሰውና ዐመድ በላያቸው ላይ ነስንሰው ገና ዱሮ ንስሓ በገቡ ነበር!
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ተአምራት፥ በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የሐዘን ልብስ ለብሰውና ዐመድ ላይ ተቀምጠው፥ ገና ዱሮ ንስሓ በገቡ ነበር።