Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አሞጽ 1:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጢሮስ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም። የወንድማማችነትን ቃል ኪዳን በማፍረስ፣ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ ለኤዶም ሸጣለችና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በምርኮ የሄዱትን ሕዝብ ሁሉ ለኤዶምያስ አሳልፈው ሰጥተዋልና፥ የወንድማማቾችንም ቃል ኪዳን አላስታወሱምና ስለ ሦስት የጢሮስ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የጢሮስ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ የገቡበትን የወንድምነት ቃል ኪዳን አፍርሰው የማረኳቸውን ሕዝቦች ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የሰ​ሎ​ሞን ምር​ኮ​ኞ​ችን በኤ​ዶ​ም​ያስ ዘግ​ተ​ዋ​ልና፥ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ንም ቃል ኪዳን አላ​ሰ​ቡ​ምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢ​ሮስ ኀጢ​አት አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምርኮኞችን ሁሉ ለኤዶምያስ አሳልፈው ሰጥተዋልና፥ የወንድሞችንም ቃል ኪዳን አላሰቡምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢሮስ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 1:9
23 Referencias Cruzadas  

በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልክተኞችን ላከ፤ እንዲሁም የዝግባ ዕንጨት፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችና ድንጋይ ጠራቢዎችን ዐብሮ ሰደደ፤ እነርሱም ለዳዊት ቤተ መንግሥት ሠሩለት።


ጌባል፣ አሞንና አማሌቅ፣ ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋራ ሆነው ዶለቱ፤


የጢሮስንና የሲዶናን ነገሥታት ሁሉ፣ ከባሕሩ ማዶ ያሉ የጠረፍ ምድር ነገሥታትን፣


ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት፣ ተርፈውም የሚረዷቸውን ሁሉ፣ ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ፣ ቀኑ ደርሷልና። እግዚአብሔር በቀፍቶር ዳርቻ የቀሩትን፣ ፍልስጥኤማውያንን ሊያጠፋ ተነሥቷል።


ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤


የመርከብ አደጋ በሚደርስበሽ ቀን፣ ሀብትሽ፣ ሸቀጥሽና የንግድ ዕቃሽ፣ መርከብ ነጂዎችሽ፣ መርከበኞችሽና መርከብ ሠሪዎችሽ፣ ነጋዴዎችሽና ወታደሮችሽ ሁሉ፣ በመርከብ ላይ ያሉትም ሁሉ፣ ወደ ባሕሩ ወለል ይዘቅጣሉ።


ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤


በኀጢአትህና በተጭበረበረው ንግድህ ብዛት፣ መቅደስህን አረከስህ። ስለዚህ እሳት ከአንተ እንዲወጣ አደረግሁ፤ እርሱም በላህ፤ በሚመለከቱህ ሁሉ ፊት፣ በምድር ላይ ዐመድ አደረግሁህ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የኤዶም ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ ርኅራኄን በመንፈግ፣ ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፤ የቍጣውንም ነበልባል ሳይገድብ፣ መዓቱን ሳያቋርጥ አውርዶበታልና፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጋዛ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ በመውሰድ፣ ለኤዶም ሸጣለችና።


እንግዶች ሀብቱን ዘርፈው ሲሄዱ፣ ባዕዳንም በበሮቹ ሲገቡ፣ በኢየሩሳሌምም ላይ ዕጣ ሲጣጣሉ፣ በዚያ ቀን ገለልተኛ ሆነህ ተመለከትህ፣ አንተም ከእነርሱ እንደ አንዱ ሆንህ።


የእግዚአብሔር ቃል ንግር በሴድራክ ምድር ላይ ይወርድበታል፤ በደማስቆም ላይ ያርፍበታል፤ የሰዎችና የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ዐይን፣ በእግዚአብሔር ላይ ዐርፏልና።


“ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረገው ታምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን ኖሮ፣ ገና ዱሮ ማቅ ለብሰው፣ ዐመድ ነስንሰው ንስሓ በገቡ ነበር።


ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ቅጣቱ ይቀልላቸዋል።


“ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ታምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ፣ ገና ዱሮ ማቅ ለብሰው፣ ዐመድ ነስንሰው ንስሓ በገቡ ነበር።


ነገር ግን በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos