ሐዋርያት ሥራ 7:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ከአገርህ ወጥተህ፥ ከዘመዶችህ ተለይተህ፥ እኔ ወደማሳይህ አገር ሂድ’ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ከአገርህና ከወገንህ ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ከአገርህና ከዘመዶችህም ወጥተህ ወደማሳይህ ወደ ማንኛውም ምድርና፤’ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘ካገርህ ውጣ፤ ከዘመዶችህም ተለይ፤ እኔም ወደማሳይህ ሀገር ና’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ‘ከአገርህና ከዘመዶችህም ወጥተህ ወደማሳይህ ወደ ማንኛውም ምድር ና’ አለው። |
ደግሞም እግዚአብሔር አብራምን “ይህችን አገር በውርስ ለአንተ እንድሰጥህ ዑር ከምትባለው ከከለዳውያን ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ከአባቴ ቤት ወጥቼ ወደ ባዕድ አገር እንድሄድ ባዘዘኝ ጊዜ ‘በምንሄድበት ቦታ ሁሉ እኅቱ ነኝ ብትዪ ለእኔ ታላቅ ውለታ እንዳደረግሽልኝ እቈጥረዋለሁ’ ብዬአት ነበር።”
እርሱም ለአንተ ታማኝ እንደ ሆነ ተመልክተህ፥ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳንን አደረግህ፤ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ኢያቡሳውያንና ጌርጌሳውያን የሚኖሩባትንም የከነዓንን ምድር ለዘሮቹ መኖሪያ ርስት አድርገህ ልትሰጠው ቃል ገባህለት፤ አንተ ታማኝ ስለ ሆንክ ቃል ኪዳንህን አጽንተህ ጠብቀሃል።
ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም።
በዚያን ጊዜ ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ፤ አባቱ ከሞተ በኋላም እግዚአብሔር ከካራን አውጥቶ ዛሬ እናንተ ወደምትኖሩባት አገር አመጣው።
አብርሃም ወጥቶ ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ ምንም እንኳ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ለመሄድ የታዘዘው በእምነት ነው።
ከዚህም በኋላ የቀድሞ አባታችሁን አብርሃምን ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ከሚገኘው ምድር ጠርቼ፥ በከነዓን ምድር ሁሉ መራሁት፤ ዘሩንም አበዛሁለት፤ ይስሐቅንም ሰጠሁት፤