እነርሱም “እያንዳንዳችን ሕልም አየን፤ ነገር ግን የእያንዳንዳችንን ሕልም የሚተረጒም ማንም የለም” አሉት። ዮሴፍም “ሕልም የመተርጐም ችሎታ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ የእያንዳንዳችሁን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።
ሐዋርያት ሥራ 3:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጴጥሮስም ሰዎቹን ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ! በዚህ ነገር ስለምን ትደነቃላችሁ? ስለምንስ ትኲር ብላችሁ ታዩናላችሁ? እኛ በራሳችን ኀይል ወይም በራሳችን መልካም ሥራ ይህን ሰው እንዲራመድ ያደረግነው ይመስላችኋልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ በዚህ ለምን ትደነቃላችሁ? ደግሞም በእኛ ኀይል ወይም በእኛ ጽድቅ ይህ ሰው ድኖ እንዲመላለስ እንዳደረግነው በመቍጠር፣ ለምን ወደ እኛ አትኵራችሁ ትመለከታላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ! በዚህ ስለምን ትደነቃላችሁ? ወይስ በገዛ ኀይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድ እንዳደረግነው ስለምን ትኩር ብላችሁ ታዩናላችሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጴጥሮስም ሕዝቡን ባያቸው ጊዜ እንዲህ አላቸው፥ “እናንት የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ለምን ታደንቃላችሁ? እኛንስ በኀይላችንና በጽድቃችን ይህን ሰው በእግሩ እንዲሄድ እንዳደረግነው አስመስላችሁ ለምን ታዩናላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ በዚህ ስለ ምን ትደነቃላችሁ? ወይስ በገዛ ኃይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድ እንዳደረግነው ስለ ምን ትኵር ብላችሁ ታዩናላችሁ? |
እነርሱም “እያንዳንዳችን ሕልም አየን፤ ነገር ግን የእያንዳንዳችንን ሕልም የሚተረጒም ማንም የለም” አሉት። ዮሴፍም “ሕልም የመተርጐም ችሎታ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ የእያንዳንዳችሁን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።
“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! ይህን ቃል አዳምጡ፤ እናንተ ራሳችሁ እንደምታውቁት የናዝሬቱ የኢየሱስ ማንነት እግዚአብሔር በእናንተ መካከል በእርሱ አማካይነት በፈጸማቸው ታላላቅ ሥራዎች፥ ተአምራትና ምልክቶች ተረጋግጦአል።
የዳነው ሰው ከጴጥሮስና ከዮሐንስ አልለይም በማለት ይዞአቸው ሳለ ሰዎቹ ተደንቀው “የሰሎሞን መመላለሻ” ወደሚባለው ስፍራ ወደ እነርሱ ሮጠው ሄዱ፤
የአባቶቻችን የአብርሃም፥ የይስሐቅና፥ የያዕቆብ አምላክ ልጁን ኢየሱስን አከበረው፤ እናንተ ግን እርሱን በጲላጦስ ፊት አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ጲላጦስም ሊለቀው ቢፈልግ እንኳ ‘አንፈልግም’ አላችሁ።
እስቲ ደግሞ ልጠይቅ፦ እግዚአብሔር የራሱን ሕዝብ ጥሎአልን? ከቶ አልጣለውም! እኔም ራሴ እስራኤላዊ ነኝ፤ ከአብርሃም ዘር የሆንኩ የብንያም ነገድ ነኝ።
እነርሱ እስራኤላውያን ናቸው፤ እግዚአብሔርም እነርሱን ልጆቹ አደረጋቸው፤ ክብሩን ገለጠላቸው፤ ቃል ኪዳን ገባላቸው፤ ሕግን ሰጣቸው፤ እውነተኛውን የአምልኮ ሥርዓት አሳያቸው፤ የተስፋውንም ቃል ሰጣቸው።