La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 27:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አሁንም መርከቡ ብቻ ይጐዳል እንጂ ከእናንተ በማንም ላይ ጥፋት አይደርስም፤ ስለዚህ አይዞአችሁ፤ አትፍሩ! ብዬ እመክራችኋለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም ቢሆን አይዟችሁ፤ መርከቧ እንጂ ከእናንተ አንዲት ነፍስ እንኳ አትጠፋምና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሁንም አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ፤ ይህ መርከብ እንጂ ከእናንተ አንድ ነፍስ እንኳ አይጠፋምና።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሁ​ንም እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ መር​ከ​ባ​ችን እንጂ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችን አንድ ሰው ስንኳ አይ​ጠ​ፋ​ምና አት​ፍሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁንም፦ አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ፤ ይህ መርከብ እንጂ ከእናንተ አንድ ነፍስ እንኳ አይጠፋምና።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 27:22
14 Referencias Cruzadas  

ከዚህም በኋላ ከዔላም ጐሣ የየሒኤል ልጅ ሸካንያ ዕዝራን እንዲህ አለው፦ “በእርግጥ እኛ በአካባቢአችን ካሉት አሕዛብ ባዕዳን ሴቶችን በማግባት በእግዚአብሔር ላይ የነበረንን እምነት አጓድለናል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ።


ሰይጣንም “በቊርበት ፈንታ ቊርበት” እንዲሉ፥ “ሰው እኮ ሕይወቱን ለማትረፍ ሲል ያለውን ሁሉ ይሰጣል።


እምነቱ ጽኑ ስለ ሆነና በእግዚአብሔርም ስለሚተማመን፥ ክፉ ወሬ አያስደነግጠውም።


በማግስቱ ሌሊት ጌታ በጳውሎስ አጠገብ ቆሞ “አይዞህ በኢየሩሳሌም እንደ መሰከርክልኝ፥ እንዲሁም በሮም ልትመሰክርልኝ ይገባሃል” አለው።


ስለዚህ እናንተ ሰዎች አይዞአችሁ! እግዚአብሔር ይህንን የነገረኝን ሙሉ በሙሉ እንደሚፈጽም አምነዋለሁ።


በዚህ ጊዜ ጳውሎስ መቶ አለቃውንና ወታደሮቹን “እነዚህ መርከበኞች በመርከቡ ላይ ዐርፈው ካልተቀመጡ እናንተ ለመዳን አትችሉም” አላቸው።


ስለዚህ እህል እንድትቀምሱ እለምናችኋለሁ። ይህም ብርታት ይሰጣችኋል፤ ከቶ ምንም ዐይነት ጒዳት አይደርስባችሁም።”


በዚህ ጊዜ ሁሉም ተጽናኑና ምግብ በሉ።


የቀሩት ደግሞ በሳንቃዎችና በመርከቡ ስብርባሪዎች ላይ ሆነው እንዲወጡ አዘዘ፤ በዚህ ሁኔታ ሁሉም በደኅና ወደ ምድር ደረሱ።


ሰዎቹ ሁሉ በሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው መማረክ ምክንያት ተማርረው ስለ ነበረ በድንጋይ ሊወግሩት በመነጋገራቸው ዳዊት በታላቅ አደጋ ላይ ነበር። እርሱ ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አጽናና፤