ሐዋርያት ሥራ 22:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በጠፍር ወጥረው ሊገርፉት ሲዘጋጁ ጳውሎስ አጠገቡ የቆመውን የመቶ አለቃ “የሮም ዜግነት ያለውን ሰው ያለ ፍርድ ልትገርፉት ተፈቅዶላችኋልን?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስም በጠፍር ወጥረው ሊገርፉት ሲሉ፣ አጠገቡ የቆመውን የመቶ አለቃ፣ “አንድን የሮም ዜጋ ያለ ፍርድ ለመግረፍ ሕግ ይፈቅድላችኋልን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጠፈርም በገተሩት ጊዜ ጳውሎስ በአጠገቡ የቆመውን የመቶ አለቃ “የሮሜን ሰው ያለ ፍርድ ትገርፉ ዘንድ ተፈቅዶላችኋልን?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊገርፉትም በአጋደሙት ጊዜ ጳውሎስ በአጠገቡ የነበረውን የመቶ አለቃ፥ “የሮማን ሰው ያለ ፍርድ ልትገርፉ ይገባችኋልን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጠፈርም በገተሩት ጊዜ ጳውሎስ በአጠገቡ የቆመውን የመቶ አለቃ፦ የሮሜን ሰው ያለ ፍርድ ትገርፉ ዘንድ ተፈቅዶላችኋልን? አለው። |
የመቶ አለቃውና ከእርሱም ጋር ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት የምድርን መናወጥና የሆነውንም ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ!” አሉ።
የመቶ አለቃው ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ! አንተ ወደ ቤቴ እንድትገባ እኔ የተገባሁ ሰው አይደለሁም፤ ነገር ግን አንዲት ቃል ብቻ ተናገር፤ አገልጋዬም ይድናል።
በቂሳርያ የሚኖር ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሮማውያን ጦር ሠራዊት ሥር “የኢጣልያ ብርጌድ” በሚባለው ውስጥ የመቶ አለቃ ነበር።
ጳውሎስ ግን “እኛ የሮም ዜጋዎች ስንሆን ያለ ፍርድ በአደባባይ ገርፈው ወደ ወህኒ አስገብተውናል። አሁን ደግሞ ከወህኒ ቤት በስውር እንድንወጣ ያደርጋሉን? አይሆንም! እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን!” ሲል መለሰ።
እኔ ግን ‘ተከሳሽ ከከሳሾች ፊት ቆሞ ለተከሰሰበት ነገር የመከላከያ መልስ ሳይሰጥ ተከሳሹን አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት አይደለም’ ብዬ መለስኩላቸው።
ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ ጳውሎስንና ሌሎችንም እስረኞች በአውግስጦስ ክፍለ ጦር ውስጥ ለነበረው ዩልዮስ ለሚባለው መቶ አለቃ አስረከቡአቸው።
የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ለማዳን ስለ ፈለገ አሳባቸውን አልተቀበለም፤ ይልቁንም መዋኘት የሚችሉ አስቀድመው ከመርከቡ ወደ ባሕር እየዘለሉ ወደ ምድር እንዲወጡ አዘዘ።