ሐዋርያት ሥራ 22:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 አዛዡ ይህን ባየ ጊዜ ጳውሎስን ወደ ወታደሮች ሰፈር እንዲያስገቡት አዘዘ፤ ሕዝቡ በእርሱ ላይ ስለምን ይህን ያኽል እንደሚጮኹ ለማወቅም እየተገረፈ እንዲመረመር አዘዘ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 የጦር አዛዡ ጳውሎስን ወደ ጦር ሰፈር እንዲያስገቡትና ሕዝቡ ለምን እንዲህ እንደሚጮኹበት እየተገረፈ እንዲመረመር ትእዛዝ ሰጠ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 የሻለቃው ወደ ሰፈሩ እንዲያገቡት አዘዘ፤ እንደዚህም የጮኹበትን ምክንያት ያውቅ ዘንድ “እየገረፋችሁ መርምሩት፤” አላቸው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 የሻለቃው የሚጮሁበት ስለ ምን እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ ወደ ወታደሮች ሰፈር እንዲያገቡትና እየገረፉ የሠራውን እንዲመረምሩት አዘዘ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 የሻለቃው ወደ ሰፈሩ እንዲያገቡት አዘዘ፥ እንደዚህም የጮኹበትን ምክንያት ያውቅ ዘንድ፦ እየገረፋችሁ መርምሩት አላቸው። Ver Capítulo |