ሐዋርያት ሥራ 22:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረገው ስላየኸውና ስለ ሰማኸው በሰው ሁሉ ፊት የእርሱ ምስክር እንድትሆን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስላየኸውና ስለ ሰማኸው ነገር በሰው ሁሉ ፊት ምስክር ትሆነዋለህና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባየኸውና በሰማኸው በሰው ሁሉ ፊት ምስክር ትሆንለታለህና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕዝብም ሁሉ ዘንድ ባየኸውና በሰማኸው ምስክር ትሆነዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባየኸውና በሰማኸው በሰው ሁሉ ፊት ምስክር ትሆንለታለህና። |
እንዲሁም ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ጌታ ኢየሱስ ወደ ሰማይ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ አብረውን ከነበሩት ከነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር እንዲሆን ያስፈልጋል።”
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም፥ በይሁዳ ምድር ሁሉ፥ በሰማርያ፥ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”
ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ያሉት ሰዎች፥ ቀጥሎም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር ሁሉ ያሉት እንዲሁም አሕዛብ ጭምር ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ አስተማርኳቸው፤ ንስሓ መግባታቸውን የሚያመለክት ነገር እንዲያደርጉም አስተማርኳቸው።
‘ጳውሎስ ሆይ! አትፍራ! በሮም ንጉሠ ነገሥት ፊት መቆም ይገባሃል! እነሆ፥ ከአንተ ጋር የሚጓዙትንም ሁሉ እግዚአብሔር ለአንተ ብሎ ከሞት ያድናቸዋል’ ብሎ ነግሮኛል።