ሐዋርያት ሥራ 2:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመገረምና በመደነቅም እንዲህ አሉ፤ “እነዚህ እንዲህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመገረምና በመደነቅም እንዲህ አሉ፤ “እነዚህ የሚነጋገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ “እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተገረሙ፤ አደነቁም፥ እንዲህም አሉ፥ “እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ፦ “እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? |
ከጥቂት ጊዜ በኋላ እዚያ ቆመው የነበሩ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ጠጋ ብለው፦ “አነጋገርህ ያስታውቃል፤ በእርግጥ አንተም ከእነርሱ አንዱ ነህ” አሉት።
ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ ተደነቀ፤ ይከተሉት የነበሩትን ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “በእውነት እላችኋለሁ፤ ይህን የሚያኽል ትልቅ እምነት ያለው አንድም ሰው በእስራኤል ስንኳ አላገኘሁም።
“ይህ ምንድን ነው? ምን ዐይነት አዲስ ትምህርት ነው? ርኩሳን መናፍስትን እንኳ በሥልጣኑ ያዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል፤” እያሉ ሁሉም በመገረም እርስ በርሳቸው ይጠያየቁ ጀመር።
ሽባውም ወዲያውኑ ተነሣና አልጋውን ተሸክሞ በሰዎቹ ሁሉ ፊት ወጣ። ስለዚህም ሰዎቹ ሁሉ ተደንቀው እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አይተን አናውቅም እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
“እናንተ የገሊላ ሰዎች፥ ስለምን ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ቆማችኋል? ይህ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፥ ወደ ሰማይ ሲያርግ ባያችሁት ዐይነት ተመልሶ ይመጣል” አሉአቸው።
“ውብ በር” እየተባለ በሚጠራው በቤተ መቅደሱ በር አጠገብ ተቀምጦ ምጽዋት ይለምን የነበረው እርሱ መሆኑን ዐወቁ፤ በእርሱ ላይም በተደረገው ነገር ይገረሙና ይደነቁ ጀመር።