ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ቤተሰቡን በመምከር ይመራቸው ዘንድ እኔ እርሱን መርጬዋለሁ፤ ልጆቹ ይህን ካደረጉ እኔም ለአብርሃም የሰጠሁትን ተስፋ ሁሉ እፈጽማለሁ።”
ሐዋርያት ሥራ 18:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ጌታ መንገድ የተማረና በመንፈስም የተቃጠለ ሆኖ ስለ ኢየሱስ በትክክል ይሰብክና ያስተምር ነበር፤ ይሁን እንጂ እርሱ የሚያውቀው የዮሐንስን ጥምቀት ብቻ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ሰው፣ የጌታን መንገድ የተማረ፣ ስለ ኢየሱስም በትክክል የሚናገርና በመንፈስ እየተቃጠለ የሚያስተምር ነበር፤ ይሁን እንጂ እርሱ የሚያውቀው የዮሐንስን ጥምቀት ብቻ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ የጌታን መንገድ የተማረ ነበረ፤ የዮሐንስንም ጥምቀት ብቻ አውቆ በመንፈስ ሲቃጠል ስለ ኢየሱስ ይናገርና በትክክል ያስተምር ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም የእግዚአብሔርን መንገድ የተማረ ነበር፤ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም ሊያስተምርና ሊመሰክር ከልቡ የሚተጋ ነበር፤ ነገር ግን የዮሐንስን ጥምቀት ብቻ ተጠምቆ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ የጌታን መንገድ የተማረ ነበረ፥ የዮሐንስንም ጥምቀት ብቻ አውቆ በመንፈስ ሲቃጠል ስለ ኢየሱስ ይናገርና በትክክል ያስተምር ነበር። |
ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ቤተሰቡን በመምከር ይመራቸው ዘንድ እኔ እርሱን መርጬዋለሁ፤ ልጆቹ ይህን ካደረጉ እኔም ለአብርሃም የሰጠሁትን ተስፋ ሁሉ እፈጽማለሁ።”
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “በየጐዳናው ቆማችሁ ተመልከቱ፤ ጥንታዊና መልካም የሆነችው መንገድ የትኛዋ እንደ ሆነች ጠይቃችሁ ተረዱ፤ ባገኛችኋትም ጊዜ በእርስዋ ሂዱ፤ በሰላምም ትኖራላችሁ።” ሕዝቡ ግን “በእርስዋ አንሄድም!” አሉ።
ጥበብ ያላቸው እነዚህን ነገሮች ይረዳሉ፤ አስተዋዮችም ያውቋቸዋል፤ የእግዚአብሔር መንገድ ትክክል ነው፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ኃጢአተኞች ግን ይሰናከሉበታል።
ቀርበውም እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፥ አንተ እውነተኛ መሆንህን እናውቃለን፤ ሰውንም በመፍራትና በይሉኝታ የምታደርገው ነገር የለም፤ የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት ታስተምራለህ፤ ታዲያ፥ ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር መክፈል ሕጋዊ ነውን? ወይስ አይደለም? እንገብር ወይስ አንገብር?”
እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፥ “እነዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው! እነርሱ የመዳንን መንገድ ያበሥሩአችኋል!” በማለት ትጮኽ ነበር።
እርሱ በድፍረት በምኲራብ መናገር ጀመረ፤ ነገር ግን ጵርስቅላና አቂላ በሰሙት ጊዜ ወደ ቤታቸው ወሰዱትና የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል አብራርተው ገለጡለት።
አንዳንዶች ግን እልኸኞች በመሆን የጌታን መንገድ በሕዝቡ ፊት እየተሳደቡ አናምንም ባሉ ጊዜ ከእነርሱ ራቀ፤ አማኞችንም ለብቻቸው ወስዶ በጢራኖስ አዳራሽ በየቀኑ ያስተምር ነበር።
የጌታንም መንገድ የሚከተሉትን ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ሲያገኝ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት የሚያስችል ደብዳቤ ለደማስቆ ምኵራቦች ተጽፎ እንዲሰጠው ሊቀ ካህናቱን ጠየቀ።
ስለዚህ እንድትፈወሱ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ እያንዳንዱም ለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ውጤት የሚያስገኝ ታላቅ ኀይል አለው፤
እንዲያውም እነዚህ የእስራኤል ሕዝብ እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው መንገዴን ይከተሉ ወይም አይከተሉ እንደሆን የማውቀው በእነዚህ ሕዝቦች መሣሪያነት በመፈተን ነው።”