ሐዋርያት ሥራ 16:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰንበትም ቀን ለጸሎት ይሰበሰቡበት ወደነበረው ከከተማው ውጪ ወደሚገኘው ወደ ወንዝ ዳር ሄድን፤ እዚያም ተቀምጠን ለተሰበሰቡት ሴቶች የእግዚአብሔርን ቃል አስተማርን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰንበት ቀንም፣ የጸሎት ስፍራ በመፈለግ፣ ከከተማዪቱ በር ወጥተን ወደ አንድ ወንዝ ወረድን፤ በዚያም ተቀምጠን ተሰብስበው ለነበሩት ሴቶች መናገር ጀመርን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰንበት ቀንም ከከተማው በር ውጭ የጸሎት ስፍራ በዚያ መሆኑን ስላሰብን ወደ ወንዝ አጠገብ ወጣን፤ ተቀምጠንም ለተሰበሰቡት ሴቶች ተናገርን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰንበት ቀንም ከከተማዉ በር ወደ ባሕሩ ዳር ወጣን፤ በዚያ የጸሎት ቤት ያለ መስሎን ነበርና፤ በዚያም ተቀምጠን፥ በዚያ ለተሰበሰቡ ሴቶች እናስተምር ጀመርን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰንበት ቀንም ከከተማው በር ውጭ የጸሎት ስፍራ በዚያ መሆኑን ስላሰብን ወደ ወንዝ አጠገብ ወጣን፤ ተቀምጠንም ለተሰበሰቡት ሴቶች ተናገርን። |
አንድ ቀን ወደ ጸሎት ቦታ ስንሄድ ወደፊት የሚሆነውን ነገር በጥንቈላ የሚያናግር ርኩስ መንፈስ ያደረባት አንዲት አገልጋይ ልጃገረድ በመንገድ አገኘችን፤ ይህች ልጃገረድ በጥንቈላዋ ለአሳዳሪዎችዋ ብዙ ትርፍ ታስገኝላቸው ነበር።
ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን እንጀራ ቈርሶ በአንድነት ለመብላት ተሰበሰብን፤ ጳውሎስ በማግስቱ መሄድ ስለ ነበረበት ለተሰበሰቡት ሰዎች ይናገር ነበር፤ ንግግሩንም እስከ እኩለ ሌሊት አስረዘመ።
እዚያ የምንቈይበት ጊዜ ሲያልቅ ተለይተናቸው ጒዞአችንን ቀጠልን፤ ሁሉም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር ሆነው እስከ ከተማው ውጪ ድረስ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ከጸለይን በኋላ ተሰነባበትን።
ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው።