ኦርዮም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች በድንኳን ሰፍረው በጦር ሜዳ ይገኛሉ፤ የቃል ኪዳኑም ታቦት ከእነርሱ ጋር ነው፤ የጦር አለቃዬ ኢዮአብና የእርሱም የጦር መኰንኖች በሜዳ ሰፍረዋል፤ ታዲያ እኔ ወደ ቤቴ ሄጄ መብላት፥ መጠጣት፥ ከሚስቴም ጋር መተኛት እንዴት ይቻለኛል? ይህን የመሰለ ነገር ከቶ እንደማላደርግ በአንተ ሕይወት እምላለሁ!”
2 ሳሙኤል 7:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ በመታደግ ካዳንኩበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ በድንኳን ውስጥ ሆኜ በየስፍራው ስዘዋወር ኖርኩ እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርኩም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ድንኳንን ማደሪያዬ አድርጌ ከቦታ ወደ ቦታ ተጓዝሁ እንጂ በቤት ውስጥ አልተቀመጥሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ ድንኳንን ማደሪያዬ አድርጌ ከቦታ ወደ ቦታ ተጓዝሁ እንጂ በቤት ውስጥ አልተቀመጥሁም የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳንና በማደሪያ እሄድና እመላለስ ነበር እንጂ በቤት አልተቀመጥሁምና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳንና በማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት አልተቀመጥሁምና አንተ የምኖርበትን ቤት አትሠራልኝም። |
ኦርዮም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች በድንኳን ሰፍረው በጦር ሜዳ ይገኛሉ፤ የቃል ኪዳኑም ታቦት ከእነርሱ ጋር ነው፤ የጦር አለቃዬ ኢዮአብና የእርሱም የጦር መኰንኖች በሜዳ ሰፍረዋል፤ ታዲያ እኔ ወደ ቤቴ ሄጄ መብላት፥ መጠጣት፥ ከሚስቴም ጋር መተኛት እንዴት ይቻለኛል? ይህን የመሰለ ነገር ከቶ እንደማላደርግ በአንተ ሕይወት እምላለሁ!”
‘ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ የሚሠራበት በመላው እስራኤል ምንም ዐይነት ከተማ አልመረጥኩም፤ አሁን ግን በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን መርጬአለሁ።’ ”
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖቶች ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔርም፦ “መኖሪያዬን በሕዝቤ መካከል አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ” ብሎ እንደ ተናገረው እኛ እያንዳንዳችን የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን።
ሰፈራችሁን በሕጉ መሠረት በንጽሕና ጠብቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ሊጠብቃችሁና በጠላቶቻችሁም ላይ ድልን ሊያጐናጽፋችሁ በሰፈራችሁ ይገኛል፤ እግዚአብሔር ፊቱን ከእናንተ እንዲመልስ የሚያደርገውን አስነዋሪ ነገር ሁሉ አታድርጉ።
ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ ሰባቱን ኮከቦች በቀኝ እጁ ከያዘውና በሰባቱ የወርቅ መቅረዞች መካከል ከሚመላለሰው የተነገረ ነው፤