በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”
2 ሳሙኤል 3:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት በሳኦል ቤተሰብና በዳዊት ቤተሰብ መካከል የሚካሄደው ጦርነት ለረጅም ጊዜ ቈየ፤ ሆኖም ዳዊት እየበረታ ሲሄድ የሳኦል ቤተሰብ እየተዳከመ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል የነበረው ጦርነት ብዙ ጊዜ ቈየ፤ ዳዊት እየበረታ ሲሄድ፣ የሳኦል ቤት ግን እየተዳከመ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል የነበረው ጦርነት ለረጅም ጊዜ ቆየ፤ ሆኖም ዳዊት እያየለ ሲሄድ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ለብዙ ጊዜ ጦርነት ሆነ፤ የዳዊት ቤት እየበረታ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ የሚሄድ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ብዙ ዘመን ጦርነት ሆነ፥ የዳዊት ቤት እየበረታ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ የሚሄድ ሆነ። |
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”
ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ስም እንደ ዕድሜአቸው ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፦ በኲሩ የኢይዝራኤል ተወላጅ ከሆነችው ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥ ሁለተኛው የቀርሜሎስ ተወላጅ ከሆነችው ከአቢጌል የተወለደው ዳንኤል፥ ሦስተኛው የገሹር ንጉሥ የታልማይ ልጅ ከሆነችው ከማዕካ የተወለደው አቤሴሎም፥ አራተኛው ከሐጊት የተወለደው አዶንያስ፥ አምስተኛው ከአቢጣል የተወለደው ሸፋጥያ፥ ስድስተኛው ከዔግላ የተወለደው ዩትረዓም፤
ለሚስቱና ለወዳጆቹም የደረሰበትን አሳፋሪ ነገር በሙሉ ነገራቸው፤ ሚስቱና እነዚያ አስተዋዮች የሆኑ ወዳጆቹም “እነሆ በገዛ እጅህ ሥልጣንህን ለመርዶክዮስ ልታስረክብ ተቃርበሃል፤ እርሱ አይሁዳዊ ስለ ሆነ ልትቋቋመው አትችልም፤ በእርግጥም እርሱ ያሸንፍሃል!” አሉት።
መርዶክዮስ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ግዛት ውስጥ በቤተ መንግሥት ከፍተኛ ሥልጣን የተሰጠው ታላቅ ሰው መሆኑና ኀይሉም እየበረታ መሄዱ በደንብ ታወቀ።
የእኛ ውጊያ ከሰዎች ጋር ሳይሆን በዚህ በጨለማ ዘመን ከሚሠሩት ገዢዎች፥ ከባለ ሥልጣኖችና ከዚህ ዓለም ኀይሎችና ይህም ማለት በሰማይ ካሉት ከርኩሳን መናፍስት ሠራዊት ጋር ነው።
እነሆ ነጭ ፈረስ አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ቀስት ይዞ ነበር፤ አክሊልም ተሰጠው፤ እርሱም ድል ነሺ ሆኖ ከድል ወደ ድል ለመሄድ ወጣ።