La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 22:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሞት ጣር ከበበኝ፤ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሞት ማዕበል ከበበኝ፤ ምናምንቴ ነገርም አጥለቀለቀኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሞት ሞገድ ከበበኝ፤ የጥፋትም ጐርፍ አጥለቀለቀኝ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሞት ጭንቅ ያዘኝ፤ የዐ​መፅ ጎር​ፍም አስ​ፈ​ራኝ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ፥

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 22:5
12 Referencias Cruzadas  

የሞት ጣር ከበበኝ፤ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ።


እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፍቅሩን በቀን ይሰጣል፤ በሌሊትም የምስጋና መዝሙር አቀርብለታለሁ፤ ወደ ሕይወቴ አምላክ እጸልያለሁ።


እርሱ በኀይለኛ ነፋስ እየተነዳ እንደሚመጣ ጐርፍ ስለ ሆነ በምዕራብ ያሉ ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም በምሥራቅ ያሉት ክብሩን ይፈራሉ።”


ጥልቅ ወደ ሆነው ወደ ባሕር መሠረት ጣልከኝ፤ በዙሪያዬም ውሃ ከበበኝ፤ ማዕበልህና ሞገድህ በላዬ ላይ አለፉ።


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ኢየሩሳሌም በጠላት ወታደሮች ተከባ ባያችሁ ጊዜ ለመጥፋት እንደ ተቃረበች ዕወቁ፤


ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።


ሰባቱን ጽዋዎች ይዘው ከነበሩት ከሰባቱ መላእክት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ እንዲህ አለኝ፦ “ና! በብዙ ውሃዎች ላይ በተቀመጠችው በታላቂቱ አመንዝራ ሴት ላይ የሚደርሰውን ፍርድ አሳይሃለሁ፤


መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “አመንዝራይቱ ተቀምጣባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ሕዝቦችና፥ ሰዎች፥ ወገኖችና የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ናቸው፤