2 ሳሙኤል 22:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላኬ ሆይ! የማዳን ጋሻህ ሰጠኸኝ፤ የአንተ ኀይልም ያጸናኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ ድጋፍህ ታላቅ አድርጎኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ ምላሽህም ታላቅ አድርጎኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመድኀኒቴንም ጋሻ ሰጠኸኝ፤ መልስህም አበዛችኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማዳንህንም ጋሻ ሰጠኸኝ፥ ተግሣጽህም አሳደገኝ። |
ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።