Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤፌሶን 6:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህም ሁሉ በላይ እንደ እሳት የሚንበለበሉትን የዲያብሎስን ፍላጻዎች ሁሉ ማጥፋት የምትችሉበትን እምነት እንደ ጋሻ አንግቡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከእነዚህም ሁሉ ጋራ፣ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከዚ​ህም ሁሉ ጋር የሚ​ን​በ​ለ​በሉ የክ​ፉን ፍላ​ፃ​ዎች ሁሉ ማጥ​ፋት እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ም​ነ​ትን ጋሻ አንሡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤

Ver Capítulo Copiar




ኤፌሶን 6:16
16 Referencias Cruzadas  

የእግዚአብሔር ስም እንደ ጠንካራ ምሽግ ነው፤ ስለዚህ ደጋግ ሰዎች ወደ እርሱ ተጠግተው ይድናሉ።


ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።


እናንተ በእምነታችሁ የጸናችሁ ስለ ሆናችሁ እናንተን ደስ እንዲላችሁ አብረናችሁ እንሠራለን እንጂ በእምነታችሁስ አናዛችሁም።


የመንፈስ ቅዱስን ሥራ አታዳፍኑ፤


በተሳለ የወታደር ፍላጻ ይወጋችኋል፤ በከሰል ፍምም ያቃጥላችኋል።


አምላኬ ሆይ! የማዳን ጋሻህ ሰጠኸኝ፤ የአንተ ኀይልም ያጸናኛል።


የሚገድሉ የጦር መሣሪያዎችን ያበጃል፤ እንደ እሳት የሚንበለበሉ ፍላጻዎችንም ያዘጋጃል።


ስለዚህ ንግግራችሁ “አዎ” ከሆነ “አዎ፥” ወይም “አይደለም” ከሆነ “አይደለም” ይሁን። ከዚህ የተረፈ ቃል ግን ከሰይጣን ነው።


እኛ ግን የብርሃን ሰዎች ስለ ሆንን ራስን በመግዛት በመጠን እንኑር፤ እምነትንና ፍቅርን እንደ ጥሩር እንልበስ፤ የመዳንን ተስፋ እንደ ራስ ቊር እንልበስ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios