እንዲሁም ለዐማሳ ሲናገር “አንተም ለእኔ የሥጋ ዘመድ ነህ፤ ከአሁን ጀምሮ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ አደርግሃለሁ፤ ይህንንም ባላደርግ እግዚአብሔር በሞት ይቅጣኝ!” ብላችሁ ንገሩት ሲል አዘዛቸው።
2 ሳሙኤል 20:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐማሣም ሊጠራቸው ሄደ፤ ነገር ግን ንጉሡ በቀጠረው ቀን ተመልሶ ሊመጣ አልቻለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሜሳይ ይሁዳን ለመጥራት ሄደ፤ ነገር ግን ንጉሡ ከወሰነው ጊዜ በላይ ቈየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አማሳይ ይሁዳን ለመጥራት ሄደ፤ ነገር ግን ንጉሡ ከወሰነው ጊዜ በላይ ቆየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሜሳይም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ይጠራ ዘንድ ሄደ፤ ነገር ግን ዳዊት የቀጠረውን ቀን አሳልፎ ዘገየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሜሳይም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ይጠራ ዘንድ ሄደ፥ ነገር ግን እርሱ የተቀጠረውን ቀን አሳልፎ ዘገየ። |
እንዲሁም ለዐማሳ ሲናገር “አንተም ለእኔ የሥጋ ዘመድ ነህ፤ ከአሁን ጀምሮ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ አደርግሃለሁ፤ ይህንንም ባላደርግ እግዚአብሔር በሞት ይቅጣኝ!” ብላችሁ ንገሩት ሲል አዘዛቸው።
ስለዚህ ንጉሡ አቢሳን “ሼባዕ ከአቤሴሎም ይበልጥ የከፋ ችግር ይፈጥርብናል፤ ወታደሮቼን ይዘህ ተከታተለው፤ አለበለዚያ የተመሸጉ ከተሞቼን ይዞ ከእኛ እጅ ሊያመልጥ ይችላል” አለው።
እንዲሁ ያደርግ ዘንድ ሳሙኤል ባዘዘው መሠረት፤ ሳኦል እስከ ሰባት ቀን ድረስ የሳሙኤልን መምጣት ሲጠብቅ ቈየ፤ ይሁን እንጂ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ሳሙኤል ወደ ጌልጌላ አልመጣም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ የሳኦል ሰዎች ሳኦልን በመክዳት ማፈግፈግ ጀመሩ፤