ሼባዕ በእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ አልፎ በመሄድ አቤልቤትማዕካ ወደተባለች ከተማ ደረሰ፤ የቢክሪ ጐሣ አባሎች የሆኑ ሁሉ ተሰብስበው ሼባዕን በመከተል ወደ ከተማይቱ ገቡ፤
2 ሳሙኤል 20:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢዮአብ ወታደሮች ሼባዕ እዚያ መሆኑን ስለ ሰሙ ሄደው ከተማይቱን ከበቡ፤ በስተውጪ በኩል ቅጽሩን አስደግፈው የዐፈር ቊልል ሠሩ፤ ቀጥሎም ቅጽሩ እንዲወድቅ ከስሩ መቈፈር ጀመሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኢዮአብ ጋራ ያለውም ሰራዊት መጥቶ፣ ሳቤዔን በአቤል ቤትመዓካ በኩል ከበበው፤ በስተ ውጭም እስከ ከተማዪቱ ግንብ ጫፍ ድረስ ዙሪያውን የዐፈር ድልድል ሠሩ፤ ግንቡን ለመናድ በኀይል በሚደበድቡበት ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኢዮአብ ጋር ያለውም ሠራዊት መጥቶ ሼባዕን በአቤል ቤት መዓካ በኩል ከበበው፤ በስተ ውጭም እስከ ከተማዪቱ ግንብ ጫፍ ድረስ ዙሪያውን የዐፈር ድልድል ሠሩ፤ ግንቡን ለመናድ በኃይል ይደበድቡት ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤተ ማካና በአቤልም መጥተው ከበቡት፤ በከተማዪቱም ላይ እስከ ቅጥርዋ ድረስ የአፈርን ድልድል ደለደሉ፤ እነርሱም ከአጥሩ ቀጥሎ ቆሙ፤ ቅጥሩንም ያፈርሱ ዘንድ ከኢዮአብ ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ተስማሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤትመዓካ ባለ በአቤልም መጥተው ከበቡት፥ በከተማይቱም ላይ እስከ ቅጥርዋ ድረስ የአፈርን ድልድል ደለደሉ፥ ቅጥሩንም ያፈርሱ ዘንድ ከኢዮአብ ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ይደባደቡ ነበር። |
ሼባዕ በእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ አልፎ በመሄድ አቤልቤትማዕካ ወደተባለች ከተማ ደረሰ፤ የቢክሪ ጐሣ አባሎች የሆኑ ሁሉ ተሰብስበው ሼባዕን በመከተል ወደ ከተማይቱ ገቡ፤
ንጉሥ ቤንሀዳድም አሳ ባቀረበው ሐሳብ ተስማምቶ የጦር አዛዦቹንና ሠራዊቱን በመላክ በእስራኤል ከተሞች ላይ አደጋ እንዲጥሉ አደረገ፤ እነርሱም ዒዮን፥ ዳን፥ አቤልቤትማዕካና የገሊላ ባሕር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች በገሊላ ባሕር አጠገብ የሚገኘውን አገርና የንፍታሌምን ግዛት ሁሉ ያዙ።
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ዒዮን፥ አቤልቤትማዕካ፥ ያኖሐ፥ ቄዴሽና ሐጾር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች፥ እንዲሁም የገለዓድን፥ የገሊላንና የንፍታሌምን ግዛቶች በመውረር ሕዝቡን ወደ አሦር ማርኮ የወሰደውም ይኸው ፋቁሔ በነገሠበት ዘመን ነበር።
እግዚአብሔር ስለ አሦራውያን ንጉሠ ነገሥት የተናገረውም ቃል ይህ ነው፦ “ሰናክሬም ወደዚህች ከተማ ፈጽሞ አይገባባትም፤ አንድ ፍላጻ እንኳ አይወረውርባትም፤ ጋሻ ያነገበ ወታደርም ወደ እርስዋ አይቀርብም፤ በዐፈር ቊልልም አትከበብም።
“ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ አሦራውያን ንጉሥ የተናገረውም ቃል ይህ ነው፤ ‘ሰናክሬም ወደዚህች ከተማ ፈጽሞ አይገባባትም፤ አንድ ፍላጻ እንኳ አይወረውርባትም፤ ጋሻ ያነገበ ወታደርም ወደ እርስዋ አይቀርብም፤ በዐፈር ቊልልም አትከበብም።
“እነሆ ባቢሎናውያን ከተማይቱን ለመያዝ ዐፈር ቈልለው ዙሪያዋን በመክበብ ላይ ናቸው፤ ጦርነት፥ ራብና ቸነፈር ከተማይቱ በእነርሱ እጅ እንድትወድቅ ያደርጓታል፤ እነሆ አንተ የተናገርከው ሁሉ መድረሱን ታያለህ፤
ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዛፎችን ቊረጡ፤ በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደምሽግ ሆኖ የሚያገለግል ዐፈር ቈልሉ፤ እርስዋ በግፍ የተሞላች ስለ ሆነ መቀጣት የሚገባት ከተማ ናት፤
ልክ እንደ አንድ ከተማ አስመስለህ በጡቡ ላይ አደጋ ለመጣል ተዘጋጅ፤ እስከ ጫፍ ድረስ የዐፈር ቊልልና መወጣጫ ሠርተህ ጡቡን በጠላት ወታደር እንደሚከበብ አስመስለህ ክበባት። በሁሉም አቅጣጫ የእንጨት ምሰሶ ሠርተህ የከተማይቱን የቅጥር በር የምታፈርስ አስመስል።