ቀጥሎም ዳዊት ለአቢሳና ለመኳንንቱ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “የራሴ ልጅ ሊገድለኝ ይፈልጋል፤ ታዲያ በዚህ ብንያማዊ ሰው ስለምን ትደነቃላችሁ? እኔን እንዲረግመኝ እግዚአብሔር ነግሮታል፤ ስለዚህ ተዉት፥ የአሰበውን ያድርግ፤
2 ሳሙኤል 18:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለኢዮአብ፥ ለአቢሳና ለኢታይም “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ በአቤሴሎም ላይ ለሞት የሚያደርስ ጒዳት እንዳታደርሱበት” የሚል ትእዛዝ ሰጣቸው፤ ዳዊት ይህን ትእዛዝ ለጦር አዛዦቹ በሰጠ ጊዜም ወታደሮቹ ሁሉ ይሰሙ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ኢዮአብን፣ አቢሳንና ኢታይን፣ “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ ልጄ በአቤሴሎም ላይ ጕዳት እንዳታደርሱበት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡ ልጁን አቤሴሎምን አስመልክቶ ለእያንዳንዱ አዛዥ ትእዛዝ ሲሰጥ ሰራዊቱ ሁሉ ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ኢዮአብን፥ አቢሳንና ኢታይን፥ “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ ልጄ በኤቤሴሎም ላይ ጉዳት እንዳታደርሱበት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡ ልጁን አቤሴሎምን አስመልክቶ ለአዛዥዎቹ ትእዛዝ ሲሰጥ ሕዝቡ ሁሉ ሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ኢዮአብንና አቢሳን ኤቲንም፥ “ለብላቴናው ለአቤሴሎም ስለ እኔ ራሩለት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡም ስለ አቤሴሎም አለቆቹን ሁሉ ሲያዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ኢዮአብንና አቢሳን ኢታይንም፦ ለብላቴናው ለአቤሴሎም ስለ እኔ ራሩለት ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡም ስለ አቤሴሎም አለቆቹን ሁሉ ሲያዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰማ። |
ቀጥሎም ዳዊት ለአቢሳና ለመኳንንቱ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “የራሴ ልጅ ሊገድለኝ ይፈልጋል፤ ታዲያ በዚህ ብንያማዊ ሰው ስለምን ትደነቃላችሁ? እኔን እንዲረግመኝ እግዚአብሔር ነግሮታል፤ ስለዚህ ተዉት፥ የአሰበውን ያድርግ፤
አቤሴሎምና እስራኤላውያን በሙሉ “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የሑሻይ ምክር ይበልጣል” አሉ፤ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ይመጣበት ዘንድ እግዚአብሔር የአኪጦፌል መልካም ምክር ተቀባይ እንዳይኖረው አደረገ።
ሰውየው ግን እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንድ ሺህ ጥሬ ብር እንኳ ብትሰጠኝ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም፤ ንጉሡ ለአንተ፥ ለአቢሳና ለኢታይ ‘ለእኔ ስትሉ በወጣቱ አቤሴሎም ላይ ለሞት የሚያደርስ ጒዳት እንዳታደርሱበት’ ሲል የሰጣችሁን ትእዛዝ ሁላችንም ሰምተናል፤
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፦ “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው!” አለ። ወታደሮቹም ዕጣ ተጣጥለው የኢየሱስን ልብስ ተከፋፈሉ።