ሙሽራ ወደ ባልዋ እንደምትመለስ ተከታዮቹ በሙሉ ወደ አንተ ተመልሰው እንዲመጡ አደርጋለሁ፤ እንግዲህ አንተ የምትፈልገው አንድ ሰው ብቻ መግደልን ነው፤ የቀረው ሌላው ሕዝብ ግን በሰላም ይኖራል።”
2 ሳሙኤል 17:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ለአቤሴሎምና ለእስራኤል መሪዎች ሁሉ ጥሩ ምክር መስሎ ታያቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክሩም አቤሴሎምንና ዐብረውት የነበሩትን የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ደስ አሠኘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክሩም አቤሴሎምንና አብረውት የነበሩትን የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ደስ አሰኘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገሩም በአቤሴሎም ፊትና በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት ደስ አሰኘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገሩም አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ደስ አሰኘ። |
ሙሽራ ወደ ባልዋ እንደምትመለስ ተከታዮቹ በሙሉ ወደ አንተ ተመልሰው እንዲመጡ አደርጋለሁ፤ እንግዲህ አንተ የምትፈልገው አንድ ሰው ብቻ መግደልን ነው፤ የቀረው ሌላው ሕዝብ ግን በሰላም ይኖራል።”
ስለዚህ ሚስቱና ወዳጆቹ ሁሉ “ርዝመቱ ኻያ ሁለት ሜትር የሆነ መስቀያ እንጨት አዘጋጅተህ ነገ ጠዋት መርዶክዮስን ለመስቀል የንጉሡን ፈቃድ መጠየቅ ትችላለህ፤ ከዚያም በኋላ ደስ ብሎህ ወደ ግብዣው ትሄዳለህ” ሲሉ ሐሳብ አቀረቡለት። ሃማንም ሐሳቡ መልካም እንደ ሆነ ተቀብሎ የመስቀያውን እንጨት አዘጋጀ።
“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ ይህን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ማድረግ ብቻም ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ሰዎች ያበረታታሉ።