እነርሱም ከሄዱ በኋላ አሒማዓጽና ዮናታን በፍጥነት ከጒድጓዱ ወጥተው በመሄድ የሆነውን ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ነገሩት፤ አኪጦፌል በእነርሱ ላይ ዐቅዶት የነበረውን ካስረዱት በኋላም “ፈጥነህ ወንዙን ተሻገር!” አሉት።
2 ሳሙኤል 17:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እርሱና አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤላውያን መሪዎች የሰጡትን ምክር ሑሻይ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ነገራቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኩሲም ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን እንዲህ አላቸው፤ “አኪጦፌል አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ምን ምን ማድረግ እንዳለባቸው መክሯቸው ነበር፤ እኔ ግን እንዲህ እንዲህ አድርጉ ብዬ መክሬአቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሑሻይ ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን እንዲህ አላቸው፥ “አኪጦፌል አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች እንዲህ እንዲህ አድርጉ ሲል መክሮአቸው ነበር፤ እኔ ግን እንዲህ እንዲህ አድርጉ ብዬ መክሬአቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርካዊው ኩሲም ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር፥ “አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህና እንዲህ መክሮአል፤ እኔ ግን እንዲህና እንዲያ መክሬአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኩሲም ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር፦ አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህና እንዲህ መክሮአል፥ እኔ ግን እንዲህና እንዲህ መክሬአለሁ። |
እነርሱም ከሄዱ በኋላ አሒማዓጽና ዮናታን በፍጥነት ከጒድጓዱ ወጥተው በመሄድ የሆነውን ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ነገሩት፤ አኪጦፌል በእነርሱ ላይ ዐቅዶት የነበረውን ካስረዱት በኋላም “ፈጥነህ ወንዙን ተሻገር!” አሉት።