ቤንሀዳድም “በሰማርያ ለያንዳንዱ ወታደር አንዳንድ ጭብጥ ዐፈር ሊዳረስ እስከማይችል ድረስ ብዙ ወታደሮችን ባላሰልፍ አማልክት ይቅሠፉኝ!” ብሎ የዛቻ መልእክቱን መልሶ ላከበት።
2 ሳሙኤል 17:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የትም ስፍራ ቢደበቅ ዳዊትን ፈልገን እናገኘዋለን፤ በረዶ በምድር ላይ እንደሚወርድ እንወርድበታለን፤ እርሱም ሆነ ከተከታዮቹ አንድ ሰው እንኳ በሕይወት የሚተርፍ አይኖርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እርሱ የገባበት ቦታ ሁሉ ገብተን አደጋ እንጥልበታለን፤ ጤዛ በመሬት ላይ እንደሚወርድ እንወርድበታለን፤ እርሱም ሆነ ሰዎቹ አንድ እንኳ አይተርፉም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም እርሱ ይገኝበታል የተባለው ቦታ ገብተን እናገኝዋለን፥ ጠል መሬት ላይ እንደሚወርድ እንወርድበታለን፤ እርሱም ሆነ ሰዎቹ አንድ እንኳ አይተርፉም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱንም ወደምናገኝበት ወደ አንድ ስፍራ እንደርስበታለን፤ ጠልም በምድር ላይ እንደሚወድቅ እንወርድበታለን፤ እርሱንና ከእርሱም ጋር ያሉ ሰዎችን ሁሉ አንድ ስንኳ አናስቀርም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱንም ወደምናገኝበት ወደ አንድ ስፍራ እንደርስበታለን፥ ጠልም በምድር ላይ እንደሚወድቅ እንወርድበታለን፥ እርሱና ከእርሱም ጋር ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ስንኳ አናስቀርም። |
ቤንሀዳድም “በሰማርያ ለያንዳንዱ ወታደር አንዳንድ ጭብጥ ዐፈር ሊዳረስ እስከማይችል ድረስ ብዙ ወታደሮችን ባላሰልፍ አማልክት ይቅሠፉኝ!” ብሎ የዛቻ መልእክቱን መልሶ ላከበት።
የልብህ ትዕቢት አታሎሃል፤ በጠንካራ አለት በተመሸገ ከተማ ውስጥ ትኖራለህ፤ የምታድርበትም ቤት በከፍተኞች ተራራዎች ላይ የተሠራ ነው፤ ‘ካለሁበት ስፍራ ማን ሊያወርደኝ ይችላል?’ በማለት ትመካለህ።
ከሞት የተረፉትም የእስራኤል ሕዝብ በብዙ ሕዝቦች መካከል እግዚአብሔር እንደሚልከው ጠልና በሣር እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ፤ ተማምነው የሚጠባበቁት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ብቻ ይሆናል።
የሚሸሸግባቸውን ስፍራዎች በትክክል አግኙ፤ ያገኛችሁትንም ማስረጃ ወዲያው ይዛችሁልኝ ኑ፤ ከዚያም በኋላ እኔ አብሬአችሁ እሄዳለሁ፤ አሁንም በዚያው ግዛት ውስጥ የሚኖር ከሆነ መላውን የይሁዳ ግዛት ማሰስ ቢያስፈልገኝም እንኳ እርሱን በማደን እይዘዋለሁ።”