በዚያን ጊዜ አኪጦፌል የሚሰጠው ማንኛውም ምክር ልክ እንደ እግዚአብሔር ቃል ተቀባይነት አግኝቶ ነበር፤ ቀድሞ ዳዊት አሁን ደግሞ አቤሴሎም የእርሱን ምክር ይከተሉ ነበር።
2 ሳሙኤል 17:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቈይ አኪጦፌል አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ዛሬ ማታ ዳዊትን አሳድጄ ለመያዝ እችል ዘንድ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች እንድመርጥ ፍቀድልኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አኪጦፌልም፣ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሰው መርጬ፣ በዛሬዪቱ ሌሊት ዳዊትን አሳድደዋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አኪጦፌልም፥ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰው ልምረጥና፥ ዛሬ ሌሊት ተነሥቼ ዳዊትን አሳድደዋለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አኪጦፌልም አቤሴሎምን አለው፥ “ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ልምረጥና በዚህች ሌሊት ተነሥቼ ዳዊትን ላሳድድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አኪጦፌልም አቤሴሎምን፦ አሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ልምረጥና በዚህች ሌሊት ተነሥቼ ዳዊትን ላሳድድ። |
በዚያን ጊዜ አኪጦፌል የሚሰጠው ማንኛውም ምክር ልክ እንደ እግዚአብሔር ቃል ተቀባይነት አግኝቶ ነበር፤ ቀድሞ ዳዊት አሁን ደግሞ አቤሴሎም የእርሱን ምክር ይከተሉ ነበር።
ደክሞት ተስፋ በመቊረጥ ላይ ሳለ ድንገተኛ አደጋ እጥልበታለሁ፤ በዚያን ጊዜ እርሱ ድንጋጤ ላይ ይወድቃል፤ ተከታዮቹም ጥለውት ይሸሻሉ ንጉሡንም ለብቻው አግኝቼ እገድለዋለሁ፤