2 ሳሙኤል 16:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዳዊትም “ይህ ሁሉ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “ንጉሥ ሆይ! አህዮቹን ያመጣኋቸው ቤተሰብህ እንዲቀመጡባቸው፥ ዳቦውና ፍራፍሬውም ለተከታዮችህ ስንቅ እንዲሆኑና የወይን ጠጁም በምድረ በዳ በሚደክሙበት ጊዜ እንዲጠጡት ነው” ሲል መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ሲባን፣ “ይህን ሁሉ ያመጣኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ሲባም “አህዮቹን የንጉሡ ቤተ ሰዎች እንዲቀመጡባቸው፣ እንጀራውንና በለሱን ወጣቶቹ እንዲበሉት፣ የወይን ጠጁን ደግሞ በምድረ በዳ የደከሙት እንዲጠጡት ነው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ጺባን፥ “ይህን ያመጣኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “አህዮቹን የንጉሡ ቤተሰቦች እንዲቀመጡባቸው፥ ዳቦውንና ፍራፍሬውን ወጣቶቹ እንዲበሉት፥ የወይን ጠጁን ደግሞ በምድረ በዳ የደከሙት እንዲጠጡት ነው” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሲባን፥ “ይህ ለአንተ ምንድን ነው?” አለው። ሲባም፥ “አህዮቹ የንጉሥ ቤተ ሰቦች ይቀመጡባቸው ዘንድ፥ እንጀራውና ተምሩም ብላቴኖቹ ይበሉት ዘንድ፥ የወይን ጠጁም በበረሃ የሚደክሙት ይጠጡት ዘንድ ነው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሲባን፦ ይህ ምንድር ነው? አለው። ሲባም፦ አህዮቹ የንጉሥ ቤተ ሰቦች ይቀመጡባቸው ዘንድ፥ እንጀራውና በለሱ ብላቴኖቹ ይበሉት ዘንድ፥ የወይን ጠጅም በበረሀ የሚደክሙት ይጠጡት ዘንድ ነው አለ። |
ዔሳውም “እፊት እፊትስ እየተነዳ ሲሄድ ያየሁት የእንስሶች መንጋ ምንድን ነው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እርሱ በአንተ ፊት ሞገስ እንዳገኝ የላክሁልህ ነው” አለ።
የዳዊት ተከታዮች ወጥተው በሄዱ ጊዜ ሕዝቡ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ንጉሡ ከተከታዮቹ ጋር የቄድሮንን ወንዝ ተሻገረ፤ በአንድነትም ሆነው ወደ በረሓው አመሩ።
መፊቦሼትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ንጉሥ ሆይ፥ እንደምታውቀው እኔ ሽባ ነኝ፤ ከአንተ ጋር ለመሄድ ፈልጌ አገልጋዬን ‘በቅሎዬን ጫንልኝ’ ብለው ከድቶኝ ሄደ፤
በሠላሳ አህዮች ላይ ተቀምጠው የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በገለዓድ ምድር ሠላሳ ከተሞች ነበሩአቸው፤ እነዚህም ከተሞች እስከ ዛሬ የያኢር መንደሮች ተብለው ይጠራሉ፤
እናንተ ኮርቻ በተጫኑ በነጫጭ አህዮች ላይ ተቀምጣችሁ የምትጓዙ፥ እናንተ በምቹና በአማረ ግላስ ላይ የምትንደላቀቁ፥ እናንተ በእግር የምትንሸራሸሩ፥ ስለዚህ ነገር ተናገሩ።
ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ “እኛ ሁላችን በራብ ደክመን ዝለናል፤ አባትህ ግን ‘በዛሬው ዕለት ምንም ዐይነት ምግብ የሚመገብ ሰው የተረገመ ይሁን’ ሲል በብርቱ አስጠንቅቆናል” አለው።