Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 15:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የዳዊት ተከታዮች ወጥተው በሄዱ ጊዜ ሕዝቡ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ንጉሡ ከተከታዮቹ ጋር የቄድሮንን ወንዝ ተሻገረ፤ በአንድነትም ሆነው ወደ በረሓው አመሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ሕዝቡ ሁሉ በሚያልፍበትም ጊዜ ባላገሩ በሙሉ እየጮኸ አለቀሰ፤ ንጉሡም የቄድሮንን ሸለቆ ተሻገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ተሻግሮ ወደ ምድረ በዳው ተጓዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ሕዝቡ ሁሉ በሚያልፍበትም ጊዜ ባላገሩ በሙሉ እየጮኸ አለቀሰ፤ ንጉሡም የቄድሮንን ወንዝ ተሻገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ተሻግሮ ወደ ምድረ በዳው አመሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ሀገ​ሪ​ቱም ሁላ በታ​ላቅ ድምፅ አለ​ቀ​ሰች። ሕዝ​ቡም ሁሉ በቄ​ድ​ሮን ወንዝ ተሻ​ገሩ፤ ንጉ​ሡም ደግሞ የቄ​ድ​ሮ​ንን ወንዝ ተሻ​ገረ፤ ንጉ​ሡና ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተሻ​ገሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በአገርም የነበሩት ሁሉ በታላቅ ድምፅ አለቀሱ፥ ሕዝቡም ሁሉ ተሻገሩ፥ ንጉሡም ደግሞ የቄድሮንን ፈፋ ተሻገረ፥ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ መንገድ ተሻገሩ።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 15:23
12 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ዳዊትም “ይህ ሁሉ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “ንጉሥ ሆይ! አህዮቹን ያመጣኋቸው ቤተሰብህ እንዲቀመጡባቸው፥ ዳቦውና ፍራፍሬውም ለተከታዮችህ ስንቅ እንዲሆኑና የወይን ጠጁም በምድረ በዳ በሚደክሙበት ጊዜ እንዲጠጡት ነው” ሲል መለሰ።


ኢየሱስ ይህን ካለ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ቄድሮን ሸለቆ ማዶ ሄደ፤ እዚያ ወደነበረውም የአትክልት ቦታ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ገባ።


ከከተማይቱ ወጥተህ የቄድሮንን ወንዝ ተሻግረህ ብትገኝ በእርግጥ ትሞታለህ፤ ለደምህም ተጠያቂ ራስህ ነህ።”


ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።


ሕፃኑም አደገ፤ በመንፈስም ጠነከረ፤ ለእስራኤል ሕዝብ እስከ ታየበት ጊዜ ድረስ በበረሓ ኖረ።


“ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፥ ጥርጊያውንም አቅኑ!’ እያለ በበረሓ የሚጮኽ ሰው ድምፅ” ብሎ ነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ስለ ዮሐንስ ነበር።


በዚያን ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ በረሓ እየሰበከ መጣ።


ካህናቱም ቤተ መቅደሱን ለማንጻት ወደ ውስጡ ገቡ፤ ያልነጻውንም ነገር ሁሉ ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ አወጡት፤ ሌዋውያኑም ከዚያ አንሥተው ከከተማ ውጪ በመውሰድ በቄድሮን ሸለቆ ጣሉት።


አያቱ ማዕካ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ አጸያፊ ጣዖት ስለ ሠራች ከእቴጌነት ሻራት፤ የሠራችውንም ጣዖት ሰባብሮ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ በእሳት አቃጠለው።


ዳዊትም “መልካም ነው! እንግዲህ ጒዞህን ቀጥል!” አለው፤ ስለዚህም ኢታይ ከወታደሮቹ ሁሉና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ጒዞውን ቀጠለ፤


እኔም ከአንተ ወሬ እስከማገኝ ድረስ በበረሓው ውስጥ በሚገኘው በወንዙ መሸጋገሪያ ላይ እጠባበቃለሁ።”


በድንና ዐመድ የሚጣልበት መላው ሸለቆ በምሥራቅ በኩል እስከ ፈረስ በር ድረስ እንኳ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከተማይቱም እንደገና ከቶ አትፈርስም፤ አትደመሰስምም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios