La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 3:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሞአብ ንጉሥ ሜሻዕ በግ አርቢ ነበር፤ በየዓመቱም አንድ መቶ ሺህ ጠቦትና የአንድ መቶ ሺህ በጎች ጠጒር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ ሞሳ በግ ያረባ ነበር፤ እርሱም መቶ ሺሕ ጠቦትና የመቶ ሺሕ አውራ በግ ጠጕር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሞዓብ ንጉሥ ሜሻዕ በግ አርቢ ነበር፤ በየዓመቱም አንድ መቶ ሺህ ጠቦትና የአንድ መቶ ሺህ በጎች ጠጉር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ ሞሳ ባለ በጎች ነበር፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ መቶ ሺህ የጠ​ጕር አውራ በጎ​ች​ንና መቶ ሺህ ጠቦ​ቶ​ችን ይገ​ብ​ር​ለት ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሞዓብም ንጉሥ ሞሳ በግ አርቢ ነበረ፤ ለእስራኤልም ንጉሥ የመቶ ሺህ ጠቦትና የመቶ ሺህ አውራ በጎች ጠጕር ይገብርለት ነበር።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 3:4
11 Referencias Cruzadas  

አብራም ብዙ እንስሶች፥ ብዙ ብርና ወርቅ ያለው ሀብታም ሰው ነበረ።


ቀጥሎም ንጉሥ ዳዊት ሞአባውያንን ድል አደረገ፤ እስረኞቹ በመሬት ላይ እንዲጋደሙ አድርጎ ከየሦስቱ ሰዎች ሁለት ሁለቱ በሞት እንዲቀጡ አደረገ። ስለዚህም ሞአባውያን የእርሱ ተገዢዎች በመሆን ይገብሩለት ነበር።


ከዚያም በኋላ በግዛታቸው ውስጥ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ሶርያውያንም ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ገበሩለት፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን እንዲቀዳጅ አደረገው።


ሞአባውያንንም ድል ነሥቶ እንዲገብሩለት አደረገ።


በምዕራባዊ ኰረብቶች ግርጌና በሜዳዎች ላይ ብዙ የቀንድ ከብቶች ስለ ነበሩትም በገጠር የተመሸጉ መጠበቂያ ግንቦችን ሠራ፤ ብዙ ጒድጓዶችንም ማሰ፤ ግብርና ይወድ ስለ ነበረ በኰረብታማ አገሮችና በለሙ ቦታ የወይን ተክል ተካዮችና ገበሬዎች ነበሩት።


በሀብትም በኩል ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ አህዮች ነበሩት፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ካሉት ሰዎች ሁሉ እርሱን የሚያኽል ሀብታምና ታላቅ ሰው አልነበረም።


እግዚአብሔር የኢዮብን የመጨረሻ ሕይወት ከመጀመሪያው አስበልጦ ባረከው፤ ስለዚህ ኢዮብ ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፤ ስድስት ሺህ ግመሎች፤ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፤ አንድ ሺህ እንስት አህዮች ነበሩት።


ሞአብ መታጠቢያዬ ነው፤ ኤዶም የእኔ መሆኑን ለማረጋገጥ ጫማዬን አኖርበታለሁ፤ በፍልስጥኤማውያንም ላይ።”