‘የቀድሞ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ያከማቹት በቤተ መንግሥትህ ያለው ሀብት ሁሉ ተጠራርጎ ወደ ባቢሎን የሚወስድበት ጊዜ ይመጣል፤ ምንም ነገር አይቀርም፤
2 ነገሥት 24:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ባገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት ይሁዳን ስለ ማጥፋት የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ወራሪ ቡድኖች ባቢሎናውያንን፥ ሶርያውያንን፥ ሞአባውያንንና ዐሞናውያንን በኢዮአቄም ላይ አስነሣበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም በኢዮአቄም ላይ ባቢሎናውያን፣ ሶርያውያን፣ ሞዓባውያንና አሞናውያን አደጋ ጣዮችን ላከበት፤ በአገልጋዮቹ በነቢያቱ አማካይነት በተነገረው በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ይሁዳን ያጠፉ ዘንድ እነዚህን ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ባገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት ይሁዳን ስለ ማጥፋት የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ወራሪ ቡድኖች ባቢሎናውያንን፥ ሶርያውያንን፥ ሞአባውያንንና ዐሞናውያንን በኢዮአቄም ላይ አስነሣበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የከለዳውያንን አደጋ ጣዮች፥ የሶርያውያንንም አደጋ ጣዮች፥ የሞዓባውያንንም አደጋ ጣዮች፥ የአሞንንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደደበት፤ በባሪያዎቹ በነቢያት ቃል እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ያጠፉት ዘንድ በይሁዳ ላይ ሰደዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የከለዳውያንንና የሶርያውያንን የሞዓባውያንንም የአሞንንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደደበት፤ በባሪያዎቹ በነቢያት እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ያጠፉት ዘንድ በይሁዳ ላይ ሰደዳቸው። |
‘የቀድሞ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ያከማቹት በቤተ መንግሥትህ ያለው ሀብት ሁሉ ተጠራርጎ ወደ ባቢሎን የሚወስድበት ጊዜ ይመጣል፤ ምንም ነገር አይቀርም፤
“እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ የይሁዳ ንጉሥ ባነበበው መጽሐፍ ውስጥ በተጻፈው መሠረት በዚህች ቦታና በሕዝብዋ ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ።
ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በእስራኤል ላይ ያደረግኹትን ነገር ሁሉ በይሁዳም ላይ አደርጋለሁ፤ ይኸውም የይሁዳን ሕዝብ ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ የመረጥኳትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና ስሜ በዚያ ይጠራል ብዬ የነበረውንም ቤተ መቅደስ እተዋለሁ።”
ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ ለእነርሱ ታላቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ ከበሉና ከጠጡም በኋላ ወደ ሶርያ ንጉሥ መልሶ ላካቸው፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሶርያውያን በእስራኤል ምድር ላይ ወረራ ማድረጋቸውን አቆሙ።
ስለዚህም የአሦር ሠራዊት ይሁዳን እንዲወር እግዚአብሔር ፈቀደ፤ ሠራዊቱም ምናሴን ማርኮ በአፍንጫው ሥናጋ በማግባት በሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው።
ይኸኛው መልእክተኛ ተናግሮ ሳይጨርስ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፥ “በሦስት ቡድን የተከፈሉ የከለዳውያን ዘራፊዎች በድንገት አደጋ ጣሉብን፤ ግመሎቹን በሙሉ ወሰዱአቸው፤ አገልጋዮችህንም በሙሉ በሰይፍ ገደሉአቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው።
እነርሱም በምድር ዳርቻ ከሚገኙ ከሩቅ አገሮች የመጡ ናቸው፤ እግዚአብሔር አገሪቱን በሞላ ለማጥፋት የቊጣ መሣሪያ የሆነ ሠራዊቱን አሰልፎአል።
“እነሆ እግዚአብሔር እስራኤል ከይሁዳ ከተለየበት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቀውን የመከራ ዘመን በአንተና በሕዝብህ፥ በአባትህም ንጉሣዊ ቤተሰብ ላይ ያመጣል፤ ይኸውም የአሦርን ንጉሥ ያመጣብሃል ማለት ነው።
የመረጥኳቸው ሕዝቤ በሁሉ አቅጣጫ በጭልፊቶች እንደ ተከበበች ወፍ ሆነዋል፤ ስለዚህ ሌሎችም የዱር አራዊት መጥተው ሥጋቸውን በመብላት እንዲደሰቱ ጥሩአቸው።
የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ በአራተኛው ዓመት እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ተናገረኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ነበር፤
‘እነሆ በስተሰሜን ወዳሉት ነገዶችና አገልጋዬ ወደ ሆነው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መልእክተኛ እልካለሁ፤ ይሁዳንና በውስጥዋ የሚኖሩትን፥ እንዲሁም በጐረቤት ያሉትን ሕዝቦች ይወጉ ዘንድ አመጣቸዋለሁ፤ ይህችን አገር ከነጐረቤቶችዋ አጠፋለሁ፤ ለማየት የሚያስፈሩና መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ ለዘለዓለም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
በቂርያትይዓሪም የሚኖር የሸማያ ልጅ ኡሪያ የተባለ ሌላም ሰው ነበር፤ ይህ ሰው ልክ እንደ ኤርምያስ በዚህች ከተማና በዚህች ምድር ላይ ጥፋት እንደሚመጣ በእግዚአብሔር ስም ትንቢት ተናግሮ ነበር፤
ባለመታዘዛችሁ የምትቀጥሉበት ከሆነ በሴሎ ያደረግኹትን ሁሉ በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ ደግሜ አደርጋለሁ፤ የዓለም ሕዝብ ሁሉ የዚህችን የከተማ ስም እንደ መራገሚያ ይቈጥራል።”
ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መጥቶ አገሪቱን በወረረ ጊዜ ከባቢሎናውያንና ከሶርያውያን ሠራዊት ሸሽተን እናመልጥ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ለመምጣት ወስነናል፤ አሁንም በኢየሩሳሌም የምንኖረው ስለዚህ ነው።”
“ጽዮን እጆችዋን ትዘረጋለች፤ ነገር ግን ማንም የሚያጽናናት የለም፤ ጐረቤቶቹ ሁሉ የያዕቆብ ዘር ጠላቶች እንዲሆኑ እግዚአብሔር አዟል። ኢየሩሳሌምም በመካከላቸው እንደ ርኩስ ነገር ሆናለች።
ባቢሎናውያንንና ከለዳውያንን ሁሉ አመጣለሁ፤ የፈቆድን፥ የሾዐንና የቆዐንን ወንዶች እንዲሁም አሦራውያንን ሁሉ አመጣለሁ፤ ወጣትነት ያላቸው፥ መልከ ቀና የሆኑ መሳፍንትና የጦር መኰንኖች፥ ታላላቅ ባለሥልጣኖችና ከፍተኛ ማዕርግ ያላቸው እነዚህ ሁሉ በፈረስ ተቀምጠው ይመጣሉ።
ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ ቤተ መቅደሱም የተሠራበት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ይሆናል።
እነሆ እነዚያን ጨካኞችና ችኲሎች ባቢሎናውያንን አስነሣባችኋለሁ፤ እነርሱ የራሳቸው ያልሆነውን ምድር ሁሉ በጦር ኀይል ለመያዝ በየሀገሩ ይዞራሉ።