2 ነገሥት 6:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ ለእነርሱ ታላቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ ከበሉና ከጠጡም በኋላ ወደ ሶርያ ንጉሥ መልሶ ላካቸው፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሶርያውያን በእስራኤል ምድር ላይ ወረራ ማድረጋቸውን አቆሙ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ስለዚህ ታላቅ ግብዣ አዘጋጅቶላቸው ከበሉና ከጠጡ በኋላ አሰናብቷቸው ወደ ጌታቸው ሄዱ። የሶርያ አደጋ ጣዮችም የእስራኤልን ምድር ለመውረር ከዚያ በኋላ አልተመለሱም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ ለእነርሱ ታላቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ ከበሉና ከጠጡም በኋላ ወደ ሶርያ ንጉሥ መልሶ ላካቸው፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሶርያውያን በእስራኤል ምድር ላይ ወረራ ማድረጋቸውን አቆሙ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ብዙም መብል አዘጋጀላቸው፤ በበሉና በጠጡ ጊዜም አሰናበታቸው፤ እነርሱም ወደ ጌታቸው ሄዱ። ከዚያም በኋላ የሶርያውያን አደጋ ጣዮች ዳግመኛ ወደ እስራኤል ሀገር አልመጡም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ብዙም መብል አዘጋጀላቸው፤ በበሉና በጠጡ ጊዜም አሰናበታቸው፤ እነርሱም ወደ ጌታቸው ሄዱ። ከዚያም በኋላ የሶርያ አደጋ ጣዮች ወደ እስራኤል አገር አልመጡም። Ver Capítulo |
ከዚያም በኋላ እነዚያ አራት ሰዎች ለእስረኞቹ ከምርኮው አስፈላጊውን ነገር ሁሉ እንዲሰጡ ተመደቡ፤ እነርሱም ራቊታቸውን ለቀሩት እስረኞች ልብስና ጫማ፥ እንዲሁም በቂ ምግብና ውሃ ሰጡአቸው፤ በቊስላቸውም ላይ የወይራ ዘይት በማፍሰስ ርዳታ አደረጉላቸው፤ በእግር ለመሄድ የማይችሉትን ደካሞችንም በአህያ ላይ አስቀመጡአቸው፤ እስረኞቹም ሁሉ በይሁዳ ግዛት ወደምትገኘው፥ የዘንባባ ዛፍ በብዛት ወደሚገኝባት ወደ ኢያሪኮ ከተማ መልሰው ወሰዱአቸው፤ ከዚህም በኋላ እስራኤላውያን ወደ መኖሪያ ከተማቸው ወደ ሰማርያ ተመለሱ።