ዳዊት፥ አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በዐመፅ መተባበሩን በሰማ ጊዜ “እግዚአብሔር ሆይ! የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት እንድትለውጥበት እለምንሃለሁ!” ሲል ጸለየ።
2 ነገሥት 19:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ስለ አሦር ንጉሠ ነገሥት ስለ ሰናክሬም ዛቻ ያቀረብከውን ጸሎት ሰምቻለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በአሦር ንጉሥ በሰናክሬም ላይ ወደ እኔ ያቀረብኸውን ልመና ሰምቻለሁ’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ስለ አሦር ንጉሠ ነገሥት ስለ ሰናክሬም ዛቻ ያቀረብከውን ጸሎት ሰምቻለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሞጽም ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ ላከ፥ “የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ የለመንኸውን ሰምቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሞጽም ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ ላከ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ የለመንኽውን ሰምቻለሁ። |
ዳዊት፥ አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በዐመፅ መተባበሩን በሰማ ጊዜ “እግዚአብሔር ሆይ! የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት እንድትለውጥበት እለምንሃለሁ!” ሲል ጸለየ።
አኪጦፌል የሰጠው ምክር ተቀባይነት እንዳላገኘ በተረዳ ጊዜ አህያውን ጭኖ ወደ መኖሪያ ከተማው ተመልሶ ሄደ፤ ሁሉን ነገር መልክ በማስያዝ ካስተካከለም በኋላ ተሰቅሎ ሞተ፤ በቤተሰቡም መቃብር ተቀበረ።
“ሕዝቤን ወደሚመራው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ተመልሰህ በመግባት እንዲህ በለው፦ ‘እኔ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም ተመልክቻለሁ፤ እኔ እፈውስሃለሁ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤
ከዚያ በኋላ ትጸልያላችሁ፤ እኔም ጸሎታችሁን እሰማለሁ፤ የእርዳታ ጩኸት ትጮኻላችሁ፤ እኔም አለሁ እላችኋለሁ፤ እናንተ የጭቈናን ቀንበር ብታስወግዱ፥ የጣት ጥቆማንና የተንኰልን ንግግር ብታቆሙ፥
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ ከአሁን በፊት የማታውቃቸውን ተመርምሮ ሊደረሰባቸው የማይችሉትን ታላላቅ ነገሮች እገልጥልሃለሁ።
ትኲር ብሎ ወደ መልአኩ ተመለከተና በመደንገጥ “ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?” አለ። መልአኩም እንዲህ አለው፦ “ጸሎትህና ለድኾች የምታደርገው ምጽዋት መልካም መታሰቢያ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ዐርጓል፤