ለዕቃ ግምጃ ቤቱም ኀላፊነት ካህኑን ሼሌምያን፥ የሕግ ምሁሩን ሳዶቅንና ሌዋዊውን ፐዳያን መደብሁ፤ የማታንያ የልጅ ልጅ የሆነው የዛኩር ልጅ ሐናንም የእነርሱ ረዳት ነበር፤ እነዚህም ሰዎች ለሥራ ጓደኞቻቸው የሚሆነውን መተዳደሪያ ለማከፋፈል ታማኞች ነበሩ።
2 ነገሥት 12:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ በደልና ስለ ኃጢአት መሥዋዕት የሚከፈለው ገንዘብ ግን ለካህናቱ ጥቅም የሚውል እንጂ ወደ ቤተ መቅደሱ ሣጥን ውስጥ አይገባም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ በደል መሥዋዕትና ስለ ኀጢአት መሥዋዕት የሚቀርበው ገንዘብ ግን የካህናቱ በመሆኑ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አይገባም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ በደልና ስለ ኃጢአት መሥዋዕት የሚከፈለው ገንዘብ ግን ለካህናቱ ጥቅም የሚውል እንጂ ወደ ቤተ መቅደሱ ሣጥን ውስጥ አይገባም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ በደልና ስለ ኀጢአት መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚያመጡት ገንዘብም ለካህናት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሠራተኞችም ይከፍሉ ዘንድ ገንዘቡን የሚወስዱትን ሰዎች አይቆጣጠሩአቸውም ነበር፤ በታማኝነት ይሠሩ ነበርና። |
ለዕቃ ግምጃ ቤቱም ኀላፊነት ካህኑን ሼሌምያን፥ የሕግ ምሁሩን ሳዶቅንና ሌዋዊውን ፐዳያን መደብሁ፤ የማታንያ የልጅ ልጅ የሆነው የዛኩር ልጅ ሐናንም የእነርሱ ረዳት ነበር፤ እነዚህም ሰዎች ለሥራ ጓደኞቻቸው የሚሆነውን መተዳደሪያ ለማከፋፈል ታማኞች ነበሩ።
እጁንም በፍየሉ ራስ ላይ ጭኖ፥ ከመሠዊያው በስተ ሰሜን በኩል ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች በሚታረዱበት ስፍራ በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ይረደው፤ ይህም ኃጢአትን የሚያስወግድ መሥዋዕት ይሆናል።
“ስለ ኃጢአት ስርየት በሚቀርበው መሥዋዕትና ስለ በደል ስርየት በሚቀርበው መሥዋዕት መካከል ለሁለቱም የሚሠራ አንድ ዐይነት ሕግ አለ፤ ይኸውም የእንስሳው ሥጋ መሥዋዕቱን ለሚያቀርበው ካህን ምግብ እንዲሆን ይሰጣል፤
“እስራኤላውያን ለእኔ የሚያቀርቡአቸውን ልዩ ስጦታዎች ሁሉ ለእናንተ፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻችሁ ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም ከእናንተና ከዘሮቻችሁ ሁሉ ጋር የምገባው የማይሻር የጨው ቃል ኪዳን ነው።”