Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 12:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ስለ በደል መሥዋዕትና ስለ ኀጢአት መሥዋዕት የሚቀርበው ገንዘብ ግን የካህናቱ በመሆኑ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አይገባም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስለ በደልና ስለ ኃጢአት መሥዋዕት የሚከፈለው ገንዘብ ግን ለካህናቱ ጥቅም የሚውል እንጂ ወደ ቤተ መቅደሱ ሣጥን ውስጥ አይገባም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስለ በደልና ስለ ኃጢአት መሥዋዕት የሚከፈለው ገንዘብ ግን ለካህናቱ ጥቅም የሚውል እንጂ ወደ ቤተ መቅደሱ ሣጥን ውስጥ አይገባም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ስለ በደ​ልና ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ያ​መ​ጡት ገን​ዘ​ብም ለካ​ህ​ናት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ለሠራተኞችም ይከፍሉ ዘንድ ገንዘቡን የሚወስዱትን ሰዎች አይቆጣጠሩአቸውም ነበር፤ በታማኝነት ይሠሩ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 12:16
9 Referencias Cruzadas  

ለዕቃ ቤቶቹም ካህኑን ሰሌምያን፣ ጸሓፊውን ሳዶቅንና ፈዳያ የተባለውን ሌዋዊ ኀላፊ አድርጌ ሾምሁ፤ መደብሁ፤ እንዲሁም የመታንያን ልጅ፣ የዛኩርን ልጅ ሐናንን ረዳታቸው አደረግሁ፤ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ታማኞች ነበሩ። ሥራቸውም ለወንድሞቻቸው የተመደበውን ቀለብ ማከፋፈል ነበረ።


የሕዝቤ ኀጢአት ለመብል ሆኖላቸዋል፤ ርኩሰታቸውንም እጅግ ወደዱ።


እጁንም በፍየሉ ራስ ላይ ይጫን፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበትም ስፍራ በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ ይህም የኀጢአት መሥዋዕት ነው።


እጁን ለኀጢአት መሥዋዕት በቀረበችው ፍየል ራስ ላይ ይጫን፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራም ይረዳት።


“ ‘የኀጢአት መሥዋዕትና የበደል መሥዋዕት አቀራረብ ሥርዐት አንድ ነው፤ መሥዋዕቶቹ የስርየቱን ሥርዐት ለሚያስፈጽመው ካህን ይሰጣሉ።


እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ከተቀደሰ ቍርባን የሚለየው ሁሉ ለአንተ፣ ለወንድና ለሴት ልጆችህ መደበኛ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም በእግዚአብሔር ፊት ለአንተና ለዘሮችህ ዘላለማዊ የጨው ኪዳን ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos