La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 11:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም በኋላ እርሱ፥ የጦር አለቆች፥ የንጉሡ ክብር ዘብና የቤተ መንግሥቱ ዘብ ጠባቂዎች ንጉሡን ከቤተ መቅደስ እስከ ቤተ መንግሥት አጅበው እንዲሄዱና ሕዝቡም ሁሉ ከኋላ እንዲከተል አደረገ፤ ኢዮአስም በዘብ ጠባቂዎች ቅጽር በር በኩል ገብቶ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም መቶ አለቆቹን፣ ካራውያንንና ዘበኞቹን እንዲሁም የአገሩን ሕዝብ በሙሉ በመያዝ ሁሉም በአንድነት ሆነው፣ ንጉሡን ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወስደው በዘብ ጠባቂዎች ቅጥር በር በኩል ታች ወዳለው ቤተ መንግሥት ይዘውት ገቡ፤ ንጉሡም በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚህም በኋላ እርሱ፥ የጦር አለቆች፥ የንጉሡ ክብር ዘብና የቤተ መንግሥቱ ዘብ ጠባቂዎች ንጉሡን ከቤተ መቅደስ እስከ ቤተ መንግሥት አጅበው እንዲሄዱና ሕዝቡም ሁሉ ከኋላ እንዲከተል አደረገ፤ ኢዮአስም በዘብ ጠባቂዎች ቅጽር በር በኩል ገብቶ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መቶ አለ​ቆ​ቹ​ንና ኮራ​ው​ያ​ንን፥ ዘበ​ኞ​ች​ንና የሀ​ገ​ሩ​ንም ሕዝብ ሁሉ ወሰ​ዳ​ቸው፤ ንጉ​ሡ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አወ​ጣው፤ በዘ​በ​ኞ​ችም በር መን​ገድ ወደ ንጉሡ ቤት አመ​ጡት፤ በነ​ገ​ሥ​ታ​ቱም ዙፋን አስ​ቀ​መ​ጡት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

መቶ አለቆቹንና ካራውያንንም፥ ዘበኞችንና የአገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፤ ንጉሡንም ከእግዚአብሔር ቤት አወረዱት፤ በዘበኞችም በር መንገድ ወደ ንጉሡ ቤት አመጡት፤ በነገሥታቱም ዙፋን ተቀመጠ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 11:19
13 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜ የምድያም ሰዎች እስማኤላውያን ዮሴፍን በግብጽ አገር ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር ከፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ የሆነ የዘበኞቹ አለቃ ነበር።


ወደ ንጉሥ ዳዊት ገብተሽ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ነግሦ በዙፋኔ ይቀመጣል’ ብለህ ለአገልጋይህ በመሐላ ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? ታዲያ፥ አሁን አዶንያስ እንዴት ሊነግሥ ቻለ? ብለሽ ንገሪው”።


እነርሱንም ለመተካት ንጉሥ ሮብዓም ጋሻዎችን ከነሐስ አሠርቶ የቤተ መንግሥቱን ቅጽር በር የመጠበቅ ኀላፊነት ባላቸው የዘብ አለቆች እንዲጠበቁ አደረገ፤


በዚህ ዐይነት ሰሎሞን በአባቱ እግር ተተክቶ እግዚአብሔር ባጸናው ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ እርሱም ሁሉ ነገር የተሳካለት ንጉሥ ሆነ፤ መላውም የእስራኤል ሕዝብ ታዘዙለት፤


ዮዳሄ ያልነጻ ማንኛውም ሰው ወደ ቤተ መቅደስ እንዳይገባ በቤተ መቅደሱ ቅጽር በሮች ሆነው የሚጠብቁ ዘበኞችን መድቦ ነበር።


የጦር መኰንኖቹ፥ የታወቁ የአገር ሽማግሌዎች የመንግሥት ባለሥልጣኖችና የቀሩትም ሕዝብ ሁሉ ከዮዳሄ ጋር በመሆን ከቤተ መቅደስ እስከ ቤተ መንግሥት ድረስ ንጉሡን አጅበው ሄዱ፤ በቤተ መንግሥቱም ዋና በር ገቡ፤ ንጉሡም በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤


ሌላው አንድ ሦስተኛ እጅ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቅ፤ የመጨረሻው አንድ ሦስተኛ እጅ የመሠረት ቅጽር በር ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ ይጠብቅ፤ ሕዝቡም ሁሉ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ውስጥ ይሰብሰቡ፤


በዳዊት ዙፋን ላይ የተቀመጡ ነገሥታት ከባለ ሥልጣኖቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በሮች ይገባሉ፤ እነርሱም ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ሕዝብ ጋር በአንድነት ሆነው በፈረሶችና በሠረገሎች ላይ ይቀመጣሉ፤ የኢየሩሳሌም ከተማ ሁልጊዜ በሕዝብ የተሞላች ትሆናለች።


“ይህ ሰው ልጆቹን ሁሉ አጥቶ ኑሮው የማይሳካለት እንዲሆን ተፈርዶበታል፤ የዳዊትን ዙፋን ለመውረስ በይሁዳ የሚነግሡ ዘሮች አይተርፉለትም ብለሽ መዝግቢ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ልክ እኔ እንዳዘዝኳቸው ብታደርጉ፥ የዳዊት ዘሮች ከዙፋናቸው አይወርዱም፤ እንደ ወትሮው ሁሉ ከመኳንንቱና ከሕዝቡ ጋር በሠረገሎችና በፈረሶች ላይ በመቀመጥ በዚህ ቤተ መንግሥት የቅጽር በሮች መግባት ትችላላችሁ።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ የሰው ልጅ በክብር ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት በአዲሱ ዓለም የእኔ ተከታዮች የሆናችሁ፥ እናንተም፥ በዐሥራ ሁለት ዙፋኑ ላይ ትቀመጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።


“የሰው ልጅ በመላእክቱ ሁሉ ታጅቦ በክብር ሲመጣ በክብር ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል፤