ነገር ግን ርብቃ የዔሳውን ዕቅድ ስለ ሰማች፥ ያዕቆብን ጠርታ እንዲህ አለችው፤ “አድምጠኝ፤ ወንድምህ ዔሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ አስቦአል፤
2 ቆሮንቶስ 9:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በይሁዳ ላሉት ክርስቲያኖች ስለሚደረገው መዋጮ ልጽፍላችሁ አያስፈልግም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለቅዱሳን ስለሚደረገው አገልግሎት ልጽፍላችሁ አያስፈልግም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቅዱሳን ስለሚደረገው አገልግሎት ልጽፍላችሁ አያስፈልግም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቅዱሳን ስለሚደረገው አገልግሎት የምጽፍላችሁ ብዙ አለኝ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቅዱሳን ስለሚሆነው አገልግሎት ልጽፍላችሁ አያስፈልግምና፤ |
ነገር ግን ርብቃ የዔሳውን ዕቅድ ስለ ሰማች፥ ያዕቆብን ጠርታ እንዲህ አለችው፤ “አድምጠኝ፤ ወንድምህ ዔሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ አስቦአል፤
እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ እንዲህ በሉት፤ እኔ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ ‘አንተ በዚያ መጽሐፍ የተነገረውን ቃል ሰምተህ፥
እስራኤላውያን የወንጌልን ቃል ባለመቀበላቸው ስለ እናንተ ስለ አሕዛብ ጥቅም የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነዋል፤ ነገር ግን በምርጫ በኩል በነገድ አባቶች ምክንያት የእግዚአብሔር ወዳጆች ናቸው።
የምትጸልዩልኝም በይሁዳ ምድር ካሉት ከማያምኑ ሰዎች እጅ እንድድንና በኢየሩሳሌም ያለኝ አገልግሎትም በእግዚአብሔር ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ነው።
ከክርስቶስ የተቀበላችሁት መንፈስ በውስጣችሁ ስለሚኖር ሌላ አስተማሪ አያስፈልጋችሁም፤ እርሱ ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ የሚያስተምራችሁም እውነትን ነው እንጂ ሐሰትን አይደለም። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንዳስተማራችሁ በክርስቶስ ኑሩ።