2 ቆሮንቶስ 5:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱንም ስንለብስ ራቁታችንን ሆነን አንገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ ከለበስነው ዕራቍታችንን ሆነን አንገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከለበስነውም በኋላ ዕራቍታችንን የምንገኝ አይደለንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም። |
በዚህ እንደ ምድራዊ ድንኳን በሆነው ሥጋችን ውስጥ ስንኖር ከብደን እንቃትታለን፤ የምንቃትተውም ሞት በሕይወት እንዲለወጥ ሰማያዊውን አካል በበለጠ እንድንለብስ ነው እንጂ ከዚህ ከምድራዊ ሥጋችን ለመለየት በመፈለግ አይደለም።
“እነሆ! እኔ እንደ ሌባ በድንገት እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይሆንና ኀፍረቱን ሰዎች እንዳያዩበት ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው የተመሰገነ ነው!”
ሀብታም ለመሆን በእሳት የተፈተነውን ወርቅ ከእኔ እንድትገዛ፥ የራቊትነትህን ኀፍረት ለመሸፈን ነጭ ልብስ እንድትለብስ፥ ለማየትም እንድችል የዐይን መድኃኒት ገዝተህ እንድትቀባ እመክርሃለሁ።