2 ቆሮንቶስ 12:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ይህ ሰው ወደ ገነት እንደ ተወሰደ ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ከነሥጋው ይሁን ወይም አይሁን አላውቅም፤ እግዚአብሔር ያውቃል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ሰው በሥጋ ይሁን ወይም ከሥጋ ውጭ እኔ አላውቅም፤ እግዚአብሔር ግን ያውቃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ፤ በሥጋ ይሁን ከሥጋ ውጭ እኔ አላውቅም እግዚአብሔር ይወቀው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያን ሰው አውቀዋለሁ፤ በሥጋው ይሁን በነፍሱ እንጃ እግዚአብሔር ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ |
የክርስቶስ የሆነ አንድ ሰው ዐውቃለሁ፤ ይህ ሰው ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ተወሰደ፤ (የተወሰደውም ከነሥጋው ይሁን ወይም አይሁን አላውቅም፤ እግዚአብሔር ያውቃል።)