ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ መሰንቆና በገና እየደረደሩ፥ አታሞ እየመቱ፥ ጸናጽል እያንሿሹና እምቢልታ እየነፉ በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ለእግዚአብሔር ክብር ያሸበሽቡ ነበር።
2 ዜና መዋዕል 7:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናቱም በተመደበላቸው ቦታ ቆሙ፤ ከእነርሱም ፊት ለፊት ሌዋውያን ቆመው አስቀድሞ ንጉሥ ዳዊት አሠርቶ እግዚአብሔርን ለማመስገን ይጠቀምባቸው በነበሩት የዜማ መሣሪያዎች ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ እያሉ በመዘመር እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ካህናቱም መለከት ሲነፉ እስራኤላውያን ሁሉ ቆመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናቱም እንደ ሌዋውያኑ፣ ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔር እንዲወደስበት የሠራውንና “ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል” በማለት እግዚአብሔርን ባመሰገነ ጊዜ፣ የተቀመጠበትን የእግዚአብሔርን የዜማ መሣሪያ ይዘው በተመደበላቸው ስፍራ ቆሙ። ካህናቱ በሌዋውያኑ ትይዩ ሆነው መለከቶቻቸውን ሲነፉም እስራኤላውያን ሁሉ ቆመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናቱም በየሥርዓታቸው፥ ሌዋውያኑም ደግሞ፦ ጽኑ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ የሚለውን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ፥ ንጉሡ ዳዊት ጌታን ለማመስገን የሠራውን የጌታን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህናቱም በፊታቸው መለከት ይነፉ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ ቆመው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህናቱም በየሥርዐታቸው ሌዋውያኑም ደግሞ፥ “ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚለውን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ፥ ንጉሡ ዳዊት እግዚአብሔርን ለማመስገን የሠራውን የእግዚአብሔርን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህናቱም በፊታቸው መለከት ይነፉ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ ቆመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህናቱም በየሥርዓታቸው፥ ሌዋውያኑም ደግሞ “ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤” የሚለውን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ፥ ንጉሡ ዳዊት እግዚአብሔርን ለማመስገን የሠራውን የእግዚአብሔርን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህናቱም በፊታቸው መለከት ይነፉ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ ቆመው ነበር። |
ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ መሰንቆና በገና እየደረደሩ፥ አታሞ እየመቱ፥ ጸናጽል እያንሿሹና እምቢልታ እየነፉ በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ለእግዚአብሔር ክብር ያሸበሽቡ ነበር።
ዮዳሄ ካህናቱንና ሌዋውያኑን የቤተ መቅደሱ ሥራ ኀላፊዎች እንዲሆኑ አደረገ፤ የእነርሱም ተግባር በንጉሥ ዳዊት የተመደበላቸውን ሥራ ማከናወንና በኦሪት ሕግ መሠረት ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን መሥዋዕት ማቃጠል ነበር፤ እንዲሁም በዳዊት መመሪያ መሠረት የዜማና የበዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ኀላፊነት ተሰጥቶአቸው ነበር፤
ንጉሥ ሕዝቅያስ እግዚአብሔር በነቢዩ ጋድና በነቢዩ ናታን አማካይነት ለንጉሥ ዳዊት የሰጠውንና ዳዊትም ተግባራዊ ያደረገውን ትእዛዝ በመከተል በበገና፥ በጸናጽልና በመሰንቆ የሠለጠኑ ሌዋውያንን በቤተ መቅደሱ ውስጥ መደበ፤
ንጉሥ ሕዝቅያስ የሚቃጠለውን መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ ያሳርጉ ዘንድ አዘዘ፤ መሥዋዕቱንም ማሳረግ ሲጀምሩ ሕዝቡ የምስጋና መዝሙር አቀረበ፤ መዘምራኑም እምቢልታ መንፋትና በዳዊት የዜማ መሣሪያዎች በመታጀብ ማዜም ጀመሩ፤
መዘምራን የሆኑ ሌዋውያን ሁሉ፥ አሳፍ፥ ሄማንና ይዱታን እንዲሁም ወንዶች ልጆቻቸውና ዘመዶቻቸው ሁሉ ጥሩ የበፍታ ልብስ ለብሰው ነበር፤ ሌዋውያኑ ጸናጽልና መሰንቆ በመያዝ በስተ ምሥራቅ በኩል ከመሠዊያው አጠገብ ቆመው ነበር፤
ከእነርሱም ጋር እምቢልታ የሚነፉ አንድ መቶ ኻያ ካህናት ነበሩ፤ እነዚህ መዘምራን ሁሉ በመለከት፥ በጸናጽል፥ በበገናና በሌሎችም የሙዚቃ መሣሪያዎች እየታጀቡ፦ “ቸር ስለ ሆነ፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግኑ” በማለት በአንድ ድምፅ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር። በዚህ ጊዜ በድንገት የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጥ አንጸባራቂ ብርሃን የሞላበት ደመና የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ስለ ሞላው ካህናቱ የአምልኮ አገልግሎታቸውን ሊያከናውኑ አልቻሉም።
እስራኤላውያን እሳት ከሰማይ ሲወርድና የእግዚአብሔርም ክብር በቤተ መቅደስ ላይ ማረፉን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው፦ “እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነው!” እያሉ ሰገዱ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ።
ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዐይነት ንጉሥ ሰሎሞንና ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ።
በሙሴ መጽሐፍ በተጻፈውም መመሪያ መሠረት በኢየሩሳሌም ለተሠራው ቤተ መቅደስ አገልግሎት፥ ካህናቱን በየክፍላቸው፥ ሌዋውያኑን በየቡድናቸው አደራጁ።
እያንዳንዳቸው እምቢልታ የያዙ ሰባት ካህናት ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ቀድመው ይሂዱ፤ በሰባተኛው ቀን ካህናቱ እምቢልታ እየነፉ አንተና ወታደሮችህ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ትዞሩአታላችሁ፤