Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 6:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በሙሴ መጽሐፍ በተጻፈውም መመሪያ መሠረት በኢየሩሳሌም ለተሠራው ቤተ መቅደስ አገልግሎት፥ ካህናቱን በየክፍላቸው፥ ሌዋውያኑን በየቡድናቸው አደራጁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በሙሴ መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላክ አገልግሎት ካህናቱን በየማዕረጋቸው፣ ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው መደቧቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በሙሴም መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት በኢየሩሳሌም ባለው በእግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ካህናቱን በየማዕረጋቸው ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው መደቡአቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ካህ​ና​ቱን በየ​ማ​ዕ​ር​ጋ​ቸው፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው አቆሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በሙሴም መጽሐፍ እንደ ተጻፈው በኢየሩሳሌም ባለው በእግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ካህናቱን በየማዕርጋቸው፥ ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው አቆሙ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 6:18
10 Referencias Cruzadas  

የአሮን ልጆች የሚከተሉት ናቸው፦ አሮን አራት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር ተብለው የሚጠሩ ናቸው፤


ሻሚር በሚካ በኩል የዑዚኤል ዘር ነው፤


ንጉሥ ዳዊትና የሌዋውያን አለቆች የአሳፍን፥ የሔማንና የይዱቱን ልጆች መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸውን መዝሙር በመሰንቆ፥ በበገናና በጸናጽል እየታጀቡ እንዲዘምሩ ለዩአቸው። ለዚህ አገልግሎት የተመደቡት ሰዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦


ለፋሲካው በዓል የሚሆነው ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኋላ፥ ካህናቱ በስፍራቸውና ሌዋውያኑም በየክፍላቸው በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት ቦታ ቦታቸውን ያዙ፤


ካህናቱም በተመደበላቸው ቦታ ቆሙ፤ ከእነርሱም ፊት ለፊት ሌዋውያን ቆመው አስቀድሞ ንጉሥ ዳዊት አሠርቶ እግዚአብሔርን ለማመስገን ይጠቀምባቸው በነበሩት የዜማ መሣሪያዎች ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ እያሉ በመዘመር እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ካህናቱም መለከት ሲነፉ እስራኤላውያን ሁሉ ቆመው ነበር።


“የሌዊን ነገድ አቅርበህ ለካህኑ አሮን አገልጋዮች እንዲሆኑ መድባቸው፤


ከእስራኤላውያን ሁሉ ተለይተው ለአሮንና ለልጆቹ ያገለግሉ ዘንድ ሌዋውያንን መድባቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos