2 ዜና መዋዕል 3:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰሎሞን አባት ንጉሥ ዳዊት ቤተ መቅደስ የሚሠራበትን ስፍራ በኢየሩሳሌም በሞሪያ ተራራ ለይ አስቀድሞ አዘጋጅቶ ነበር፤ ይህም ስፍራ እግዚአብሔር ለንጉሥ ዳዊት የተገለጠበት፥ ኢያቡሳዊው ኦርና አውድማ አድርጎ ይጠቀምበት የነበረ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ላይ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ዳዊት ባዘጋጀው ቦታ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም ጌታ ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የጌታን ቤት መሥራት ጀመረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በአሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ። |
እግዚአብሔርም “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ” አለው።
የእግዚአብሔር መልአክ ኢየሩሳሌምን ለመደምሰስ በሚዘጋጅበት ጊዜ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለ መቅጣት ያለውን ውሳኔ ለውጦ ይቀሥፋቸው የነበረውን መልአክ “በቃህ! አቁም!” አለው፤ በዚህም ጊዜ መልአኩ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ላይ ቆሞ ነበር።
ዳዊትም “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና የእስራኤል ሕዝብ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርቡበት መሠዊያ ሊኖሩ የሚገባቸው በዚህ ስፍራ ነው” አለ።