2 ዜና መዋዕል 2:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስና ለራሱ ቤተ መንግሥት ለመሥራት ወሰነ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ፣ ለራሱም ቤተ መንግሥት እንዲሠራ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም ለጌታ ስም ቤተ መቅደስ፥ ለመንግሥቱም ቤተ መንግሥትን ለመሥራት አሰበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ስም ቤት፥ ለራሱም ቤተ መንግሥት ልሥራ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ስም ቤት፥ ለመንግሥቱም ቤት ይሠራ ዘንድ አሰበ። |
እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት ‘ከአንተ በኋላ የማነግሠው ልጅህ ለእኔ ቤተ መቅደስ ይሠራልኛል’ ሲል ተስፋ ሰጥቶት ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለመሥራት እነሆ፥ አሁን ወስኛለሁ፤
“እነሆ እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቆአል፤ ስለዚህም እኔ በአባቴ እግር ተተክቼ የእስራኤል ንጉሥ ሆኜአለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ቤተ መቅደስንም ሠርቼአለሁ፤
ለእኔ ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝ እርሱ ነው፤ እርሱ ልጅ ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ መንግሥቱም በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።’ ”
ከግብጽ ለሚገዛው ለያንዳንዱ ሠረገላ ስድስት መቶ ጥሬ ብር ለያንዳንዱ ፈረስ አንድ መቶ ኀምሳ ጥሬ ብር ይከፍሉ ነበር። እነርሱም መልሰው ለሒታውያንና ለሶርያ ነገሥታት ይሸጡላቸው ነበር።
ንጉሥ ኪራምም በመቀጠል፦ “ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስንና ለራሱ ቤተ መንግሥትን የሚሠራ በጥበብ፥ በማስተዋልና፥ በብልኀት የተሞላ ልጅን ለንጉሥ ዳዊት የሰጠ፥ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን!” አለ።
ከዚያም እኔ ያዘዝኳችሁን ነገር ሁሉ የምታመጡት እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ መጠሪያ ወደ መረጠው ቦታ ይሆናል፤ ይኸውም የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና ሌላውንም መሥዋዕታችሁን ሁሉ፥ ዐሥራታችሁንና መባችሁን ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የተሳላችሁትን የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን ሁሉ ታመጡለታላችሁ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ለእርሱ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በዚያ ስሙ እንዲጠራበት የሚመርጠውን ቦታ ፈልጉና ወደዚያ ሂዱ፤
“በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ ባትፈጽሙ፥ አስደናቂና አስፈሪ የሆነውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ባታከብሩ፥