Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት፥ ለራ​ሱም ቤተ መን​ግ​ሥት ልሥራ አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ፣ ለራሱም ቤተ መንግሥት እንዲሠራ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሰሎሞንም ለጌታ ስም ቤተ መቅደስ፥ ለመንግሥቱም ቤተ መንግሥትን ለመሥራት አሰበ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስና ለራሱ ቤተ መንግሥት ለመሥራት ወሰነ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ስም ቤት፥ ለመንግሥቱም ቤት ይሠራ ዘንድ አሰበ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 2:1
13 Referencias Cruzadas  

ለሰ​ሎ​ሞ​ንም ሰባ ሺህ ተሸ​ካ​ሚ​ዎች፥ ሰማ​ንያ ሺህም በተ​ራ​ራው ላይ ድን​ጋይ የሚ​ጠ​ርቡ ጠራ​ቢ​ዎች ነበ​ሩት።


እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት፦ በአ​ንተ ፋንታ በዙ​ፋ​ንህ ላይ የማ​ስ​ቀ​ም​ጠው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል ብሎ እንደ ነገ​ረው፥ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ አስ​ባ​ለሁ።


ሰሎ​ሞ​ንም የራ​ሱን ቤት በዐ​ሥራ ሦስት ዓመት ሠራ፤ የቤ​ቱ​ንም ሥራ ሁሉ ጨረሰ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አባ​ቴን ዳዊ​ትን፥ “ለስሜ ቤት ትሠራ ዘንድ በል​ብህ አስ​በ​ሃ​ልና ይህን በል​ብህ ማሰ​ብህ መል​ካም አደ​ረ​ግህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስፋ እንደ ሰጠ በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ ተነ​ሣሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዙፋን ላይ ተቀ​መ​ጥሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት ሠራሁ።


ከዚ​ህም በኋላ ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት፥ የን​ጉ​ሡን ቤትና ሰሎ​ሞን ያደ​ር​ገው ዘንድ የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ሠርቶ በፈ​ጸመ ጊዜ፥


እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል፤ ልጅም ይሆ​ነ​ኛል፤ እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።


ሄደ​ውም ከግ​ብፅ አንድ ሰረ​ገላ በስ​ድ​ስት መቶ ብር፥ አን​ድ​ንም ፈረስ በመቶ አምሳ ሰቅል ብር አመጡ፤ እን​ዲ​ሁም ለኬ​ጢ​ያ​ው​ያ​ንና ለሦ​ርያ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ በየ​ተ​ራ​ቸው ያመ​ጡ​ላ​ቸው ነበር።


የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራ​ምም ደግሞ አለ፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ለመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ቤት ይሠራ ዘንድ ጥበ​በ​ኛና ብል​ሃ​ተኛ፥ አስ​ተ​ዋ​ይም ልጅ ለን​ጉሡ ለዳ​ዊት የሰጠ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን የፈ​ጠረ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ይሁን።


በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።


ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችሁ ሁሉ በአ​ንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመ​ረ​ጠ​ውን ስፍራ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ዚ​ያም ትመ​ጣ​ላ​ችሁ።


“በዚህ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ታደ​ርግ ዘንድ፥ ይህ​ንም ክቡ​ርና ምስ​ጉን ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን ትፈራ ዘንድ ባት​ሰማ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos