አንድ ቀን አዶንያስ “ዔንሮጌል” ተብሎ በሚጠራው የውሃ ምንጭ አጠገብ የዞሔሌት አለት በሚባለው ስፍራ በጎችን፥ በሬዎችንና የሰቡ ወይፈኖችን ዐርዶ መሥዋዕት አቀረበ፤ የንጉሥ ዳዊትን ልጆችና በይሁዳ የሚገኙትን የመንግሥት ባለሥልጣኖች ሁሉ ወደዚህ ወደ መሥዋዕቱ በዓል መጥተው ተካፋዮች እንዲሆኑ ጋበዛቸው፤
2 ዜና መዋዕል 18:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጥቂት ዓመቶች በኋላም ኢዮሣፍጥ አክዓብን ለመጐብኘት ወደ ሰማርያ ከተማ ሄደ፤ አክዓብም ለኢዮሣፍጥና ለአጃቢዎቹ ክብር ብዙ በጎችንና የቀንድ ከብቶችን ዐርዶ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ አክዓብ በገለዓድ በሚገኘው በራሞት ከተማ ላይ አደጋ ለመጣል ይተባበረው ዘንድ ኢዮሣፍጥን አግባባው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥቂት ዓመታት በኋላም አክዓብን ሊጐበኝ ወደ ሰማርያ ወረደ። አክዓብም ለርሱና ዐብሮት ለነበረው ሕዝብ ብዙ በግና በሬ ዐረደ፤ ከዚያም በራሞት ገለዓድ ላይ አደጋ እንዲጥል አግባባው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጥቂት ዓመት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ። አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ ብዙ በጎችና በሬዎችን አረደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ሬማት ዘገለዓድ እንዲሄድ አባበለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጥቂት ዓመታት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ። አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ ብዙ በጎችንና በሬዎችን አረደ፤ ወደደውም፤ ከእርሱም ጋር ወደ ሬማት ዘገለዓድ ይሄድ ዘንድ አባበለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጥቂት ዓመት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ። አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ ብዙ በጎችና በሬዎችን አረደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ሬማት ዘገለዓድ ይሄድ ዘንድ አባበለው። |
አንድ ቀን አዶንያስ “ዔንሮጌል” ተብሎ በሚጠራው የውሃ ምንጭ አጠገብ የዞሔሌት አለት በሚባለው ስፍራ በጎችን፥ በሬዎችንና የሰቡ ወይፈኖችን ዐርዶ መሥዋዕት አቀረበ፤ የንጉሥ ዳዊትን ልጆችና በይሁዳ የሚገኙትን የመንግሥት ባለሥልጣኖች ሁሉ ወደዚህ ወደ መሥዋዕቱ በዓል መጥተው ተካፋዮች እንዲሆኑ ጋበዛቸው፤
በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ፥ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የያኢር ጐሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፥ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት፥ እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጽር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስድሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ፤
በዚያን ጊዜ ነቢዩ ኤልሳዕ ደቀ መዛሙርቱ ከሆኑት ነቢያት አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለ፤ “በገለዓድ ወደምትገኘው ወደ ራሞት ለመሄድ ተዘጋጅ፤ ይህንንም የዘይት ማሰሮ ያዝ፤
“በራሞት ላይ አደጋ ለመጣል ከእኔ ጋር ትዘምታለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮሣፍጥም “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ነው፤ በጦርነቱም እንተባበርሃለን አለው።
የሐናኒ ልጅ የሆነው ኢዩ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ለመገናኘት መጥቶ እንዲህ ሲል ገሠጸው፤ “አንተ ክፉዎችን መርዳትና እግዚአብሔርን ከሚጠሉት ጋር መተባበር መልካም ይመስልሃልን? ይህ ያደረግኸው ክፉ ነገር የእግዚአብሔር ቊጣ በአንተ ላይ እንዲወርድ አድርጎአል፤
ይህም ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ እኔ በኢየሩሳሌም አልነበርኩም፤ አርጤክስስ የባቢሎን ንጉሠ ነገሥት በሆነ በሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ወደ ባቢሎን ተመልሼ ሄጄ ነበር፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ከንጉሡ ፈቃድ ጠይቄ፥
ስለዚህም ለሮቤል ነገድ ከፍታ ባለው በረሓ የምትገኘው የቤጼር ከተማ፥ ለጋድ ነገድ በገለዓድ ግዛት የምትገኘው ራሞትና፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ግዛት ውስጥ የምትገኘው ጎላን እንዲለዩ አደረገ።
በምሥራቅ ዮርዳኖስ፥ ከኢያሪኮም በስተ ምሥራቅ ከፍ ብሎ በሚገኘው በረሓማ አገር፥ በሮቤል ግዛት ውስጥ የምትገኘውን ቤጼርን፥ በጋድ ግዛት ውስጥ በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ግዛት በባሳን የምትገኘውን ጎላንን መርጠው ለዩ፤