Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 18:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በሀብት በበለጸገና ዝነኛ በሆነ ጊዜ የእርሱና የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ቤተሰብ በጋብቻ እንዲተሳሰሩ አደረገ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኢዮሣፍጥ ታላቅ ሀብትና ክብር ባገኘ ጊዜ፣ ከአክዓብ ጋራ በጋብቻ ተሳሰረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለኢዮሣፍጥም ብዙ ሀብትና ክብር ነበረው፤ እርሱም ከአክዓብ ቤተሰብ ጋር በጋብቻ ትስስርን አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ለኢ​ዮ​ሣ​ፍ​ጥም ብዙ ብል​ጥ​ግ​ናና ክብር ነበ​ረው፤ ከአ​ክ​ዓ​ብም ወገን ሚስት አገባ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ለኢዮሳፍጥም ብዙ ብልጥግናና ክብር ነበረው፤ ለአክዓብም ጋብቻ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 18:1
17 Referencias Cruzadas  

በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር በማድረግ ሁለንተናውን ለኃጢአት አሳልፎ የሸጠ አክዓብን የሚምስል ማንም አልነበረም፤ ይህን ሁሉ ለማድረግ የተገደደው ሚስቱ ኤልዛቤል ወደ ክፋት ስለ መራችው ነው፤


ከዚያ ቀጥሎ ባሉት ሦስት ዓመቶች ውስጥ በእስራኤልና በሶርያ መካከል ጦርነት ተወግዶ ሰላም ሰፍኖ ነበር፤


ኢዮሣፍጥ ያደረጋቸው ነገሮችና፥ በጦርነት ላይ ያሳየው ጀግንነትም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል፤


የንጉሥ አካዝያስ እናት ዐታልያ የልጅዋን መገደል እንደ ሰማች ወዲያውኑ የይሁዳ ንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት በሙሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ ሰጠች።


ሚስቱም የአክዓብ ልጅ ስለ ነበረች እንደ አክዓብ ቤተሰብ የእስራኤል ነገሥታት ይፈጽሙት የነበረውን የክፋት መንገድ ተከተለ፤ በደል በመሥራትም እግዚአብሔርን አሳዘነ፤


ስለዚህ ኢዮሣፍጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ገናና እየሆነ ሄደ፤ በመላው ይሁዳ ምሽጎችንና፥ እጅግ የበዛ ስንቅና ትጥቅ የተከማቹባቸውን ከተማዎች ሠራ። በኢየሩሳሌምም የተለየ ችሎታ ያላቸውን ተዋጊዎች አኖረ፤


ስለዚህ እግዚአብሔር የኢዮሣፍጥ መንግሥት በይሁዳ ላይ እንዲጸና አደረገ፤ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት ያመጡለት ስለ ነበረም እጅግ የበለጸገና የከበረ ሆነ፤


ስለዚህ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ስለ መሰላቸው በእርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ከበቡት፤ ነገር ግን ኢዮሣፍጥ ጮኸ፤ እግዚአብሔር አምላክም ከእነርሱ እጅ በመታደግ አዳነው፤ እነርሱም በእርሱ ላይ አደጋ ከመጣል ተገቱ።


የሐናኒ ልጅ የሆነው ኢዩ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ለመገናኘት መጥቶ እንዲህ ሲል ገሠጸው፤ “አንተ ክፉዎችን መርዳትና እግዚአብሔርን ከሚጠሉት ጋር መተባበር መልካም ይመስልሃልን? ይህ ያደረግኸው ክፉ ነገር የእግዚአብሔር ቊጣ በአንተ ላይ እንዲወርድ አድርጎአል፤


በአንድ ወቅት ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ብዙ ክፉ ነገር ከፈጸመው ከእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ ጋር የስምምነት ውል አድርጎ ነበር፤


ከአክዓብ ሴቶች ልጆች አንዲቱን በማግባቱ፥ የንጉሥ አክዓብንና የሌሎቹን የእስራኤል ነገሥታት መጥፎ ምሳሌነት ተከትሎ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአትን ሠራ፤


እናንተ ግን፥ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ የቀረው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፤


በማይመች ሁኔታ ከማያምኑ ሰዎች ጋር አትጣመሩ፤ ጽድቅና ኃጢአት እንዴት ሊተባበሩ ይችላሉ? ብርሃንና ጨለማ እንዴት አብረው ሊኖሩ ይችላሉ?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos