La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 9:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዳገቱ አድርገው ወደ ከተማው ሲወጡ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው “ባለ ራእይ እዚህ አለን?” ብለው ጠየቁአቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፣ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፣ “ባለራእዩ እዚህ ነውን?” ሲሉ ጠየቁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፥ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፥ “ባለ ራእዩ እዚህ አለን?” ሲሉ ጠየቋቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቈነ​ጃ​ጅት ውኃ ሊቀዱ ሲወጡ አገ​ኙና፥ “ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ?” አሉ​አ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በከተማይቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቆነጃጅት ውኃውን ሊቀዱ ሲወጡ አገኙና፦ ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ? አሉአቸው።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 9:11
9 Referencias Cruzadas  

እዚያ በደረሰ ጊዜ ከከተማው ውጪ ባለ የውሃ ጒድጓድ አጠገብ ግመሎቹ ተንበርክከው እንዲያርፉ አደረገ፤ ሰዓቱም ሊመሽ ተቃርቦ፥ ሴቶች ውሃ ለመቅዳት የሚወጡበት ጊዜ ነበር፤


ገና ጸሎቱን ሳይጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ መጣች፤ የዚህችም ልጅ አባት በቱኤል ይባል ነበር፤ እርሱም የአብርሃም ወንድም ናኮር ከሚስቱ ከሚልካ የወለደው ነው።


እነርሱም “እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን ይዘው እዚህ ከመሰብሰባቸው በፊት ምንም ማድረግ አንችልም፤ ሁሉም እዚህ ከመጡ በኋላ ግን ድንጋዩን በኅብረት አንከባለን በጎቹን እናጠጣቸዋለን” አሉት።


ያዕቆብም ከእረኞቹ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ወደዚያ መጣች፤ እርስዋ የበጎች እረኛ ነበረች።


አንድ የምድያም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ውሃ ለመቅዳትና በገንዳ እየሞሉ የአባታቸውን በጎችና ፍየሎች ለማጠጣት ወደዚያ መጡ።


እንደ ዐመፀኛ ሰው የጻድቁን ሰው ቤት ለመዝረፍ አትሸምቅ፤ መኖሪያውንም አትውረር።


እነሆ አድምጡ! ውሃ በሚቀዳባቸው ጒድጓዶች ዙሪያ የሚሰማው የብዙ ሰዎች ድምፅ፥ የእግዚአብሔርን ድል ያበሥራል፤ የእስራኤልንም ሕዝብ ድል አድራጊነት ይናገራል። ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ፥ ከከተሞቻቸው ተሰልፈው ወረዱ።


ሳኦልም አገልጋዩን “መልካም ነው እንሂድ!” አለው፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ሰው ወደ አለበት ከተማ ሄዱ።